ቻይና፤ አሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትሮቻቸው እንዲገናኙ ያቀረበችውን ጥያቄ ውድቅ አደረገች
ይህ ጉዳይ በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ መቃቃር የሚፈጥር ነው ተብሏል
የቀጠናዊ የደህንነት ውጥረት እና የንግድ አለመግባባት ባለበት ሁኔታ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የሁለቱ ሀገራት ስብሰባ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው
አሜሪካ በሲንጋፖር በሚካሄደው አመታዊ የደህንነት ስብሰባ ላይ የመከላከያ ሚኒስትሮች እንዲገናኙ ያቀረበችውን ጥያቄ ቻይና ውድቅ ማድረጓን የተለያዩ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ይህ ጉዳይ በሁለቱ ሀገራት መካከል አዲስ መቃቃር የሚፈጥር ነው ተብሏል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የፔንታጎን ጸኃፊ ከመከላከያ ሚኒስትር ሊ ሻንግፉ ጋር እንዲገናኙ ግንቦት መጀመሪያ ላይ ያቀረበውን ጥያቄ እንዳማትቀበል ቻይና አሳውቃናለች ብሏል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ መነጋገር አስፈላጊ መሆኑን ገልጿል።
ባለፈው ሳምንት የኋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ እንደተናገሩት ዋና ጸኃፊው ሊሎድ ኦስቲን ከቻይና አቻቸው ጋር ለመነጋገር እቅድ ተይዞ ነበር።
የቀጠናዊ የደህንነት ውጥረት እና የንግድ አለመግባባት ባለበት ሁኔታ ይደረጋል ተብሎ የነበረው የሁለቱ ሀገራት ስብሰባ ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው።
ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ በተካሄደ ስብሰባ ላይ የአሜሪካ የንግድ ጸኃፊ ጊና ራይሞንዶ እና የቻይናው የንግድ ሚኒስቴር ዋንግ ዌንታዎ በንግድና በኢንቨስትመንት ዙሪያ ተከራክረዋል።
መቀመጫውን በሲንጋፖር ያደረገ የደህንነት ተንታኝ
ቻይና ኦስቲንን ላለማግኘት መወሰኗ እየተሻሻለ በመጣው የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል ብሏል።