መከላከያ ሚኒስትሩ ሊዮድ ኦስቲን ለአራት ቀናት በጽኑ ህክምና ክትትል ውስጥ መቆየታቸው ተገልጿል
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር በጠና መታመማቸው ተገለጸ፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር መከላከያ ሚኒስትር ሊዮድ ኦስቲን በጸና ታመው ሆስፒታል መግባታቸው ተገልጿል፡፡
በሐማስ-እስራኤል ጦርነት ምክንት በመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ጫና የተፈጠረባት አሜሪካ መከላከያ ሚኒስትሯ ታመው ነበር ተብሏል፡፡
ሊዮድ ኦስቲን ለአራት ቀናት በዋልተር ሪድ የሕክምና ማዕከል በጽኑ ህክምና ክትትል ውስጥ እንደቆዩ የተገለጸ ሲሆን አሁን ላይ ጤናቸው መመለሱን ፖለቲኮ ዘግቧል፡፡
የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የመከላከያ ሚኒስትራቸው ስለመታተማቸው አለመስማታቸው ዋነኛ መነጋገሪያ የነበረ ሲሆን ይህም ሆን ተብሎ ጉዳዩን እንዳይሰሙ የተደረገ ነው ተብሏል፡፡
እንደ አሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ገለጻ ከሆነ የሊዮድ ኦስቲን መታመም ለፕሬዝዳንቱ ያልተነገረው ሚኒስትሩ መታመማቸው በሚዲያ እና ለማንኛውም ባለስልጣን እንዳይነገር በመፈለጋቸው ነው፡፡
አሜሪካ እና የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ሉዓላዊነት እንዲከበር ጠየቁ
ፕሬዝዳንት ባይደንም በትናንትናው ዕለት ከሊዮድ ኦስቲን ጋር በጉዳዩ ዙሪያ እንደተወያዩ ሲገለጽ ሚኒስትሩ ምን አጋጥሟቸው ወደ ሆስፒታል እንደገቡ እስካሁን ይፋ አልተደረገም፡፡
አሜሪካ ከቀናት በፊት በኢራቅ ባለው የሀገሪቱ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያዎች ላይ ለደረሰባት ተደጋጋሚ የአማጺያን ጥቃት እርምጃ መውሰድ ጀምራለች፡፡
ሚኒስትሩም ይህን ዘመቻ እየመሩ እያለ በጠና ታመው ወደ ሆስፒታል ሲገቡ በበዓል እረፍት ላይ የነበሩት ምክትል መከላከያ ሚኒሰትሯ ካትሊን ሂልስ ዘመቻውን እንዲመሩ ተደርጓል ተብሏል፡፡
ሊዮድ ኦስቲን እስካሁን ወደ ስራቸው እንዳልተመለሱ ሲገለጽ መቼ እንደሚመለሱም አልታወቀም፡፡