ሚንስትሩ የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን በመውጣቱም ከህግ አውጭዎች ትችት ገጥሟቸዋል
የአሜሪካ የሪፐብሊካን ም/ቤት የሀገሪቱን መከላከያ ሚንስትር ሎይድ ኦስተንን ደመወዝ ወደ 1 ዶላር ዝቅ ለማድረግ የቀረበ የውሳኔ ሃሳብን አጽድቋል።
የመከላከያ ሚንስትሩ ዓመታዊ ደመ-ወዝ 221 ሽህ ዶላር ነው።
ሪፐብሊካኖች የመከላከያ ሚኒስትሩን ደመወዝ እንዲቀነስ የቀረበውን ሃሳብ ያጸደቁት በስራቸው ደስተኛ ባለመሆናቸው ነው ተብሏል።
እርምጃው ህግ ሆኖ የመጽደቅ እድሉ አነስተኛ ነው የተባለ ቢሆንም፤ በወግ አጥባቂዎችና በመከላከያ መካከል እያደገ የመጣው ውጥረት ማሳያ ሆኗል።
የም/ቤቱ የዲሞክራት አባላት እርምጃውን በመቃወም ከፖለቲካ እይታ የዘለለ አይደለም ብለውታል።
የ2024 በጀትን የነደፉት የሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች አልወደዷቸውም የተባሉ የሌሎችን የውትድርና ሹማምንት ደመወዝንም ቀንሰዋል።
የፕሬዝዳንት ባይደን ከፍተኛ ወታደራዊ ሹም የሆኑት ሎይድ ኦስተን፤ የአሜሪካ ጦር ከአፍጋኒስታን በመውጣቱ ከህግ አውጭዎች ትችት ገጥሟቸዋል።