እገዳው እስራኤል፣ ዩክሬንን እና ቁልፍ አጋር የሚባሉ ሀገራትን አይመለከትም ተብሏል
አሜሪካ የጦር መሳሪያ ንግድን አገደች፡፡
የዓለማችን ልዕለ ሀያሏ ሀገር አሜሪካ የጦር መሳሪያ ንግድ እንዳይካሄድ ማገዷን የሐገሪቱ ንግድ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
ከአሜሪካ የጦር መሳሪያ ፋብሪካዎች ለሀገር ውስጥ እና ሌሎች ሀገራት የጦር መሳሪያዎችን በመላክ ንግድ የተማሩ ግለሰቦች እና ተቋማት በውሳኔው ማዘናቸውን አስታውቀዋል፡፡
የሀገሪቱ ንግድ ሚኒስቴር የጦር መሳሪያ ለጊዜው መታፈዱን ከመናገሩ ውጪ ለምን እንዳገደ ግልጽ አለማድረጉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የጦር መሳሪያ ንግዱ ወታደራዊ ተቋማትን ወይም መንግስታዊ አካላትን አይመለከትም የተባለ ሲሆን የጦር መሳሪያ ንግድን ለ90 ቀናት እንደታገደ ተገልጿል፡፡
እገዳው የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ እና ብሔራዊ ደህንነትን የማስጠበቅ አካል ነው የተባለ ሲሆን እንደ ዩክሬን፣ እስራኤል እና ሌሎች ቁልፍ ወዳጅ ሀገራትን እንደማይመለከት ተገልጿል፡፡
ቻይና ለአሜሪካ ሰልሏል ያለችውን ግለሰብ ከሰሰች
ለንግድ ዓላማ እንዳይዉሉ ከታገዱ የጦር መሳሪያዎች መካከል የእጅ የጦር መሳሪያን እና መነጽሮችን ይመለከታል የተባለ ሲሆን በቀጣዮቹ ሶት ወራት ውስጥ እገዳው ያመጣው ለውጥ ከተገመገመ በኋላ ሊነሳ እንደሚችል ተገልጿል፡፡
የጦር መሳሪያዎችን ወደ ውጪ ሀገራት በመላክ ይተዳደሩ የነበሩ ፋብሪካዎች እና ነጋዴዎች በእገዳው ይጎዳሉ የተባለ ሲሆን አዲስ የጦር መሳሪያ ንግድ ማውጠሰትም አብሮ ታግዷል ተብሏል፡፡
ይሁንና ለመንግስት ተቋማት የጦር መሳሪያ የሚሸጡ ነነጋዴዎች ስራቸውን መቀጠል ይችላሉ የተባለ ሲሆን ተቀባይ ሀገራትን በግልጽ ማስቀመጥ እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ ከቻሉ እገዳው እንደማይመለከታቸው ተገልጿል፡፡