ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ከሄዱ ቤጅንግ እርምጃ እንደምትወስድ ማስጠንቀቋን ተከትሎ ውጥረቱ አይሏል
የአሜሪካ አፈጉባዔ ናንሲ ፔሎሲ የእስያ ጉዟቸውን መጀመራቸውን በትናንትናው እለት ገልጸዋል፡፡
አፈጉባዔዋ ወደ እስያ ለመጓዝ ባወጡት ዕቅድ ላይ የታይዋንን ስም አለማካተታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
አፈጉባዔዋ የሩቅ ምስራቅ ጉብኝታቸውን መጀመራቸውን ገልጸው በዚህ ጉዞም ሲንጋፖርን፣ ማሌዥያን ፣ ደቡብ ኮሪያንና ጃፓን እንደሚሸፍን አስታውቀዋል።
የቻይናው ፕሬዝዳት “የታይዋን ጉዳይ በእሳት እንደመጫወት ነው” ሲሉ አሜሪከን አስጠነቀቁ
የጉዟቸው ዓላማ በአሜሪካ እና በሀገራቱ መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሆነም ገልጸዋል። ናንሲ ፔሎሲ በእስያ ጉብኝታቸው ታይዋንን እንደሚጎበኙ ቀደም ብለው ገልጸው የነበረ ቢሆንም በአሁኑ የጉዞ ዝርዝር ግን ታይዋን አልጠቀሱም።
አፈጉባዔዋ በጉዞ ታይዋንን ያልጠቀሱት ከቻይና በተሰነዘረ የማስፈራሪያ ዛቻ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል። ናንሲ ፔሎሲ ወደ ታይዋን ከሄዱ ቤጅንግ እርምጃ እንደምትወስድ ማስጠንቀቋን ተከትሎ ውጥረቱ አይሏል።
ቻይና በታይዋን ጉዳይ እንደማትደራደር በተደጋጋሚ ስትገልጽ አሜሪካ ደግሞ ታይዋንን የሚነካ ብሔራዊ ጥቅሜን የነካ ነው እያለች ነው።
ከሰሞኑ የስልክ ውይይት ያደረጉት የቻይና እና የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች በጭቅጭቅ የተሞላ ውይይት አድርገዋል።
የሁለቱ ፕሬዝዳንቶች የንግግር ርዕስ ታይዋን የነበረች ቢሆንም በተለመደ ያለመስማማት መንፈስ ንግግራቸውን ጨርሰዋል ተብሏል።