አሜሪካ ከ50 አመታት በኋላ መንኮራኩር በጨረቃ ደቡብ ዋልታ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳረፈች
መሬት ላይ የነበሩ ኢንጂነሮች በመንኮራኩሯ 'የአውቶኖመስ ናቪጌሽን ሲስተም' ላይ አጋጥሞ የነበረው ችግር ለመፍታት በ11ኛው ሰአት ጥረት አድርገዋል።
ያልተጠበቀውን የሬድዮ የግንኙነት መቋረጥ ለመመለስ እና ከመሬት 384ሺ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለችውን መንኮራኩር እጣ ፈንታ ለመወሰን ጥቂት ጊዜ ፈጅቷል
አሜሪካ ከ50 አመታት በኋላ መንኮራኩር በጨረቃ ደቡብ ዋልታ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ አሳረፈች።
በአሜሪካ ቴክሳስ ግዛት በሚገኘው 'ኢንቲዩቲቭ ማሽንስ' በተባለው ኩባንያ የተሰራችው እና የበረረችው የጠፈር መንኮራኩር በጨረቃ ደቡብ ዋልታ ላይ በትናትናው እለት ማረፏን ሮይተርስ ዘግቧል።
በግል ኩባንያ የተሰራችው መንኮራኩር በጨረቃ ደቡብ ዋልታ ላይ ማረፏ፣ ለአሜሪካ ከግማሽ ክፍለዘመን በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።
የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ማዕከል ናሳ የመንኳራኩራ በተሳካ ሁኔታ ማረፍ፣ በዚያ ያሉ ጠፈርተኞቹ በዚህ አስርት አመት መጨረሻ ሲመለሱ ለሳይንስ ጥናት የሚውሉ መንኮራኩሮችን ለመላክ ለተያዘው እቅድ ትልቅ ስኬት ነው ሲል አድንቀዋል።
ነገርግን መንኮራኩሯ ከማረፏ በፊት አጋጥሞ የነበረው የኮሙኒኬሽን ችግር መንኳራኩሯ የጎደላት ነገር ይኖር ይሆን የሚል ጥያቄ አስነስቶ ነበር።
ባለስድስት እግር የሮቦት ማረፊያ ያላት እና ሰው አልባ የሆነችው 'ኦዲሰስ' የተሰኘችው መንኮራኩር (23:23 ጂኤሞቲ) ላይ ማረፍ መቻሏን ኩባንያው እና ናሳ ሆውስተን በሚገኘው የመቆጣጠራያ ጣቢያ ሆነው በሰጡት የጋራ መግለጫ አስታውቀዋል።
መሬት ላይ የነበሩ ኢንጂነሮች በመንኮራኩሯ 'የአውቶኖመስ ናቪጌሽን ሲስተም' ላይ አጋጥሞ የነበረውን ችግር ለመፍታት በ11ኛው ሰአት ጥረት አድርገዋል።
ያልተጠበቀውን የሬድዮ የግንኙነት መቋረጥ ለመመለስ እና ከመሬት 384ሺ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ያለችውን መንኮራኩር እጣ ፈንታ ለመወሰን ጥቂት ጊዜ ፈጅቷል።
በመጨረሻ ግንኙነት ሲመለስ፣ መንኮራኩራ ማረፏ ሊረጋገጥ ችሏል።
"መሳሪያዎቻችን በጨረቃ ገጽ ላይ አርፈዋል፤ ስለዚህ እንኳን ደስ አላችሁ"ሲሉ የኢንቲዩቲቭ ማሽንስ ሚሽን ዳይሬክተር ቲም ክሬን ተናግረዋል።
ኩባንያው ቆየት ብሎ በኤክስ ገጹ ላይ የበረራ መቆጣጠሪያዎቹ "ኦዲሰስ መቆሟን እና መረጃ መላክ መጀመሯን" ማረጋገጣቸውን ገልጿል።