ፖለቲካ
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በፊት በጠፈር ተመራማሪዎች የተሰበሰበ ጠጠር የጨረቃን እድሜ አሳየ
በአፖሎ ተልዕኮ ከጨረቃ 110.4 ኪ.ግ የአፈር እና የድንጋይ ናሙና ለተጨማሪ ጥናት ወደ መሬት መጥቷል

ተመራማሪዎች ጨረቃ ከዚህ ቀደም ከታሰበው በ40 ሚሊዮን ዓመታት ትበልጣለች ብለዋል
በጎርጎሮሳዊያኑ 1972 "አፖሎ 17" በሚል ስያሜ በተደረገው ተልዕኮ ናሙና የተወሰደው የጠጠር ድንጋይ የጨረቃ እድሜ ከሚገመተው በላይ መሆኑን ጠቁሟል።
በተልዕኮው የአሜሪካ የጠፈር ተመራማሪዎች ሃሪሰን ሽሚት እና ዩጂን ሰርናን ከጨረቃ 110.4 ኪ.ግ የአፈር እና የድንጋይ ናሙናዎችን ለተጨማሪ ጥናት ወደ መሬት ይዘው ተመልሰዋል።
ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ ተመራማሪዎች ስለ ጨረቃ አፈጣጠር እና ትክክለኛ እድሜ ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ እየሰጡ ነው።
በዚህም ተመራማሪዎች ጨረቃ ከዚህ ቀደም ከታሰበው በ40 ሚሊዮን ዓመታት ያህል ትበልጣለች ብለዋል።
የጨረቃ እድሜ 4.46 ቢሊዮን ዓመት እንደሆነ ተመራማሪዎች ይናገራሉ።
የጨረቃ እድሜንና አፈጣጠርን በተመለከተ መሪ መላምት ቢኖርም ትክክለኛ የተፈጠረችበትን ጊዜ ማወቅ ግን አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።
ተመራማሪዎቹ ከግዙፉ ተጽዕኖ በኋላ በተፈጠረ ጠጣር ንጥረ-ነገሮች እድሜን ለማረጋገጥ እንደ ዘዴ ተጠቅመዋል ተብሏል።
ጨረቃ በአማካይ በ385 ሽህ ኪሎ ሜትር እርቀት ላይ በምድር ላይ ትዞራለች።