ህንድ በጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ መንኮራኩር በማሳረፍ በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በቪዲዮ ኮንፈረንስ የመንኮራኩሯን ማረፍ ተመልክተዋል
ቻንድራያን-3 የተሰኘችው መንኮራኩር የውሃ ክምችት ሊኖርበት ይችላል በሚባለው የጨረቃ ክፍል በሰኬት ማረፍ ችላለች
ህንድ በጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ የጠፈር መንኮራኩር በማሳረፍ የመጀመሪያዋ ሀገር መሆን ችላለች።
ቻንድራያን-3 የተሰኘችው መንኮራኩር የውሃ ክምችት ሊኖርበት ይችላል በሚባለው የጨረቃ ክፍል በሰኬት ማረፍ መቻሏን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
ከአንድሃራ ፕራደሽ የጠፈር ጣቢያ የተተኮሰችው መንኮራኩራ ከስድስት ሳምንታት በኋላ ጨረቃ ላይ አርፋለች።
የመንኮራኩሯ በስኬት ማረፍ በሳቲሽ ዳዋኖ የስፔስ ማዕከል የነበሩ የተልኮውን የሚያስፈጽሙ ሰራተኞች አስደስቷቸዋል።
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ናሬንድራ ሞዲ በቪዲዮ ኮንፈረንስ የመንኮራኩሯን ማረፍ ተመልክተዋል።
ሞዲ ለስፔስ ምርምር ድርጅት ባደረጉት የደስታ ንግግር "ይህ የ1.4 ቢሊዮን ህዝብ የልብ ትርታ ነው። ይህች አዲሷ ህንድ ነች። አዲስ ጅምር እና የአዲስ አስተሳሰብ ጥረት ውጤት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።
ሞዲ እንደገለጹት የመንኮራኩሯ ጨረቃ ላይ ማረፍ መንግስት የገባውን ቃል በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል።
ሞዲ የህንድ በጨረቃ ደቡባዊ ዋልታ ላይ መንኮራኩራ ማሳረፍ የመላው ዓለም ስኬት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
በሽዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሬስቶራንቶች፣ በሱቆች፣ በቢሮ እና በቤታቸው ተሰባስበው የመንኮራኩሯን ማለፍ ተከታትለዋል።