በአሜሪካ የሚመራው ግብረኃይል በቀይ ባህር ቅኝት ማድረግ ጀመረ
በባብ ኤል ማንዴብ ዘኩል በሚያለፉ መርከቦች ላይ የድሮን እና የሚሳይል ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ በርካታ የመርከብ ድርጅቶች የቀይ ባህር መስመር መጠቀም አቁመዋል
በኢራን የሚታገዙት የሀውቲ ታጣቂዎች ማንኛውንም አለምአቀፍ ትብብር መግጠም እንደሚችሉ ተናግረዋል
በአሜሪካ የሚመራው ግብረኃይል በቀይ ባህር ቅኝት ማድረግ ጀመረ።
በአሜሪካ የሚመራው እና በርካታ ሀገሪት የተሳተፉበት ግብረ ኃይል የንግድ መርከቦችን ደህንነት ለመጠበቅ በቀይ ባህር ላይ ቅኝት ጀምሯል።
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ልሎይድ ኦስቲን በኢራን በሚደገፉት የሀውቲ ታጣቂዎች ተደጋጋሚ የሚሳይል እና የድሮን ጥቃት ማድረጋቸውን ተከትሎ የንግድ መርከቦችን ለመጠበቅ የብዙ ሀገራት ግብረ ኃይል መቋቋሙን አስታውቀዋል።
የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ የባህር ኃይል የተቀመጠባትን ባህሬንን የጎበኙት ኦስቲን እንደገለጹት ግብረ ኃይሉ እንግሊዝን፣ ባህሬንን፣ ካናዳን፣ ፈረንሳይን፣ ጣሊያንን፣ ኔዘርላንድስ፣ ኖርዎይ እና ሲሺየልስን ይጨምራል።
ኦስቲን "ይህ አለምአቀፍ ችግር ስለሆነ የጋ ትብብር ይጠይቃል። ስለዚህ ዛሬ ብዙ ሀገራትን ያሳተፈ ወሳኝ የደህንነት ትብብር የሆነው ኦፐሬሽን ፕሮስፔሪቲ ጋርዳሪን መመስረቱን አስታውቃለሁ" ብለዋል።
በኢራን የሚታገዙት የሀውቲ ታጣቂዎች ማንኛውንም አለምአቀፍ ትብብር መግጠም እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ሀውቲዎች በቀይ ባህር ላይ በሚያልፉ መርከቦች ላይ ጥቃት የሚሰነዝሩት ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው የፍልስጤሙ ሀማስ አጋርነት ለማሳየት መሆኑን ገልጸዋል።
መርከቦች በቀይ ባህር በኩል በሚያለፍ መርከቦች ላይ ጥቃት እንደሚሰነዝሩ አስጠንቅቀውም ነበር።
የሀውቲ ታጣቂዎች በባብ ኤል ማንዴብ በኩል በሚያለፉ መርከቦች ላይ የድሮን እና የሚሳይል ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ በርካታ የመርከብ ድርጅቶች የቀይ ባህር መስመር መጠቀም አቁመዋል።