ቀይ ባህርን መጠቀም ያቆሙ ግዙፍ የመርከብ ኩባንያዎች የትኞቹ ናቸው?
የሃውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ ስጋት መደቀናቸውን ተከትሎ በርካታ መርከቦች መስመሩን እየተው ነው
የሃውቲ ታጣቂዎች ተግባር የአለማችን 10 በመቶ የንግድ መተላለፊያ የሆነውን ቀይ ባህር ውጥረት ውስጥ ከቶታል
በርካታ የንግድ መርከብ ድርጅቶች የሃውቲ ጥቃትና ዛቻን ተከትሎ ቀይ ባህርን መጠቀም ማቆማቸውን አስታውቀዋል።
ለሃማስ አጋርነታቸውን የገለጹት የሃውቲ ታጣቂዎች እስራኤል በፍልስጤማውያን ላይ የምታደርሰውን ጥቃት ካላቆመች ከቴል አቪ ጋር ግንኙነት ባላቸው መርከቦች ላይ ጥቃት እንደሚያደርስ መዛቱ ይታወሳል።
ቡድኑ የየትኛውም ሀገር መርከብ ወደ እስራኤል የሚያቀና ከሆነ በሚሳኤል እመታዋለው ማለቱም አይዘነጋም።
ከወር በፊት የብሪታንያን መርከብ ያገቱት የሃውቲ ታጣቂዎች በቅርቡ የኖርዌይ ሰንደቅ አላማ የምታውለበልብ መርከብን በክሩዝ ሚሳኤል መምታቱም የአለማችን 10 በመቶ የንግድ መተላለፊያ የሆነውን ቀይ ባህር ውጥረት ውስጥ ከቶታል።
ይህንን ተከትሎም ግዙፍ የንግድ መርከብ ኩባንያዎች መርከቦቻውን ከቀቀይ ባር መስመር እያስወጡ መሆኑን አስታውቀዋል።
የዓለማችን ግዙፉ የንግድ ምርከብ ግሩፕ ሜትድትራኒያን ሸፒንክ ኩባንያ (ኤም.ኤስ.ሲ) እየነገሰ የመጣውን ውጥር ተከትሎ መርከቦቹን ከባህር አቅጣጫ ማስወጣቱን አስታውቋል።
የፈረንሳይ የንግድ መርከብ ኩባንያ ሲ.ኤም.ኤ መርከቦቹን በቀይ ባህር መስመር ላይ ማሰማራቱን እንዳቆመ በትናትናው እልት ገልጿል።
ሜርስክ በሚል መጠሪያው የሚታወቀው ግዙፉ የዴንማርክ የንግድ መርከብ ኩባንያም በትናትናው እለት መርከቦቼን ከቀይ ባህር መስምር አስጥቻለሁ ያለ ሲሆን፤ የጀርመኑ ሃፓግ ሎልዩድ የመርከብ ኩባንያም መርከቦቹን ወደ ቀይባህር እንደማይልክ አስተሰውቋል።
ኩባንያዎቹ ከውሳኔ ላይ የደረሱት በኢራን እንደሚደገፉ የሚነገርላቸው የሃውቲ ታጣቂዎች የየትኛውም ሀገር መርከብ ወደ እስራኤል የሚያቀና ከሆነ በሚሳኤል አንደሚመቱ ማሳወቃቸውን ተከትሎ ነው።
የአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ጃክ ሱሊቫኒ ባለፈው ሳምንት አሜሪካ በቀይ ባህር የሚጓዙ መርከቦች ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚረዳ የባህር ሃይል ወታደራዊ ግብረሃይል ለማቋቋም ከሌሎች ሀገራት ጋር ንግግር እያደረገች መሆኗን መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢራን በቀይ ባህር በአሜሪካና አጋሮቿ የጋራ ወታደራዊ ግብረሃይል ለማሰማራት መታቀዱን ተቃውማለች።