መረጃዎች ለመስጥት በአጠቃላይ 14ሺ ዶላር ተቀብሏል የተባለው ዛሆ በ2009 ከቻይና ወደ አሜሪካ ከገባ ከአምስት አመት በኋላ ዜግነት አግኝቷል
የአሜሪካ የባህር ኃይል አባል ለቻይና ሚስጥር አሳልፎ በመስጠት ተከሶ ታሰረ።
የአሜሪካ የባህር ኃይል አባሉ ለቻይና ወታደራዊ መረጃዎችን እና እቅዶችን አሳልፎ በመስጠት ተከሶ መታሰሩን ሚዲያዎች ዘግበዋል።
ዌንሄንደግ ዛሆ የተባለው የ26 አመቱ ሰራተኛ ባለፈው ጥቅምት ወር ሙሰና ተቀብሎ ለቻይና ደህንነት መረጃ አሳልፎ መስጠቱን አምኗል።
ዛሆ በካሊፎርኒያ ናቫል ቤዝ ተቀጥሮ ይሰራ ነበር።
የአሜሪካ ባለስልጣናት እንደገለጹት ሰራተኛው ከ2021-2023 ስለወታደራዊ ልምምድ፣ የዘመቻ ትዕዛዝ እና ሌሎች ወሳኝ መረጃዎችን አሳልፎ ሰጥቷል።
የአሜሪካ የባህር ኃይል በኢንዶ ፖሲፊክ ቀጣና ስለሚያካሄደው መጠነ ሰፊ ልምምድ እና በጃፖኗ ኦኪናዋ ደሴት የሚገኘው የአሜሪካ ቤዝ የራዳር ሲስተምን የሚያሳይ ብሉ ፕሪንት አሳልፎ በመስጠት ተከሷል።
በኢኪናዋ የሚገኘው የአሜሪካ የባህር ኃይል ሰፈር፣ በእስያ ለምታካሂደው ወታደራዊ ዘመቻ በጣም ወሳኝ ነው።
አሜሪካ በቅርብ አመታት ውስጥ በኢንዶ ፖሲፊክ ቀጣና ያለውን የቻይናን እንቅስቃሴ ለመግታት አጋር ፍላጋዋን አጠናክራለች።
በቀጣናው ከአጋሮቿ ጋር የምታደርገውን ወታደራዊ ልምምድ እንዲጨምር አድርጋለች።
የአሜሪካ ባለስለጣናት የሌሎች ሀገራት መረጃ ተላልፍ ስለመሰጠቱ ያሉት ነገር የለም።
የሴኩሪቲ ክሊራንስ ያለው እና በፖርት ሁኔሜ በሚገኘው የባህር ኃይል ሰፈር ይሰራ የነበረው ዛሆ፣ ጥብቅ ቁጥጥር በሚደረግባቸው የወታደራዊ እና የባህር ኃይል ተቋማት ውስጥ በተደጋጋሚ ይገባ እንደነበር የአሜሪካ የፍትህ ዲፖርትመንት ገልጿል።
ዛሆ ኮድ ያላቸውን የመገናኛ ዘዴዎች ይጠቀም ነበር ተብሏል።
እነዚህን መረጃዎች ለመስጥት በአጠቃላይ 14ሺ ዶላር ተቀብሏል የተባለው ዛሆ በ2009 ከቻይና ወደ አሜሪካ ከገባ ከአምስት አመት በኋላ ዜግነት አግኝቷል።