“መንግስት ስም የሚያጠፉ ምእራባውያንን አልታገስም” ማለቱን ተከትሎ አሜሪካ ምን አለች?
የኢትዮጵያ መንግሰት አና በህወሓት መካከል ከሳምንት በፊት የተጀመረው ድርድር እንደቀጠለ ነው
ኔድ ፕራይስ፤ “የድርድሩ መራዘም ተደራዳሪዎች የተራራቀ አቋም ይዘው ለመቀመጣቸው አመላካች ነው” ብለዋል
“መንግስት ስም የሚያጠፉ ምእራባውያንን አልታገስም” ማለቱን ተከትሎ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ምለሽ ሰጥተዋል።
የኢትዮጲያ መንግስት ምእራባውያን አካላት በኢትዮጲያ መንግስት ላይ የሚያደርሱትን በሀሰት ሰም የማጥፋት ዘመቻ እንደማይታገስ መግለጹ ይታወሳል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በትናትናው እለት መግለጫ በሰጡበት ወቅት ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር።
ኔድ ፕራይስ በምለሻቸው፤ የኢትዮጵያን መንግስት መግለጫ መመልከታቸውን ገልጸው፤ “በመግለጫው ውስጥ ክሱ ትክክልኛ ነው በሚለው ላይ በዚህ ሰዓት ምንም መናገር አልችልም፤ የቀረበውን መረጃ እና አላማውን መጀመሪያ መረዳት አለብን” ሲሉ ተናግረዋል።
“ሆኖም ግን የአሜሪካ ዋነኛ ዓላማ በአፍሪካ ህብረት የሚመራው የሰላም ሂደት ከግብ እንዲደርስ ነው፤ ይህ በጣም ግልጽ ነው ሌላ ድብቅ የፖለቲካ አላማ የለውም” ሲሉም ገልጸዋል።
የአሜሪካ አለማ በጣም ግልጽ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፤ እነዚህም ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ማድረግ፣ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ሰብአዊ ርዳታ ለማድረስ፣ ሲቪሎችን ለመጠበቅ እርምጃዎችን መውሰድ እና ኤርትራ ከሰሜን ኢትዮጵያ መውጣቷን ማየት ነው ሰሉም ተናግረዋል።
“ጦርነት በሚካሄድባቸው አካባቢዎች አሳሳቢ የሰብአዊ መብት ረገጣዎች እንዳሉመረጃዎች የደርሱናል፤ ከሚደርሱን መረጃዎች ውስጥ የተወሰኑት አሳማኝ ናቸው” ያሉት ቃል አቀባዩ “ይህ አሜሪካ ህ እንደሚያሳስባት በግዳሚ ትገልጻለች፤ ግጭቱ ተዋናይ የሆኑ ሁሉም ሀይሎች ከዚህ ተግባር ሊታቀቡ ይገባል” ብለዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ስምንተኛ ከሳምንት በፊት በመንግስት እና የህወሓት መካከል እየተደረገ ስላለው ድርድር በተመለከተ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል።
ቃል አቀባዩ በመግለጫቸው በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካ ልዩ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር በድርድሩ ላይ በ“ተሳታፊነት እና በታዛቢነት” እየተካፈሉ መሆኑን ገልጸው፤ ድርድር እስከሚጠናቀቅ ድረስ በደቡብ አፍሪካ እንደሚቆዩ ተናግረዋል።
ይጠናቀቃል ተብሎ ከተያዘለት ቀነ ገደብ ያለፈው የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ድርድር መራዘም፤ ተደራዳሪዎቹ የተራራቀ አቋም ይዘው ወደ ድርድር ለመግባታቸው አመላካች ነው” ብለዋል።
ቃል አቀባዩ ኔድ ፕራይስ የድርድሩ መራዘም መንግስትና ህወሓት አብረው ለመቀመጥ ፈቃደኛ ሆነው እንደቀጠሉ ያመለክታል ያሉ ሲሆን፤ ተደራዳሪዎች በመካከላቸው ያለውን እንደሚያጠቡ ተስፋ እናደርጋለን ሲሉም ተናግረዋል።
በአፍሪካ ህብረት መሪነት በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል ባለፈው ሳምንት ሰኞ በደቡብ አፍሪካ የተጀመረው ድርድር እንቀጠለ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከሲጂቲኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ግጭቱን በሰላም የመፍታቱ ሂደት “ብዙ ጣልቃገብነት” እንዳጋጠመው ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ ጉዳይ “በግራ በቀኝ ብዙ ጣልቃገብነት” መኖሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ “ኢትዮጵያውያን መረዳት ያለባቸው የራሳችንን ጉዳይ በራሳችን መፍታት አንደምንችል” ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሰት አና በህወሓት መካከል የሰላም ንግግሩ ቢጀመርም ጦርነቱ አሁንም እየቀጠለ ነው።
በድጋሚ ነሀሴ አጋማሽ ላይ በተቀሰቀሰው ጦርነት የህወሓት ሃይሎች እስከ ቆቦ ድርስ መግባት እና የተወሰኑ ቦታዎች መቆጣጠር ችለው የነበረ ቢሆን የኢትዮጵያ መንግስት መልሶ መቆጣጠር ችሏል።
ጦርነቱ አሁን የቀጠለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ሽሬ፣አላማጣ እና ኮረምን እና ሌሎች ቁልፍ የትግራይ ከተሞችን መቆጣጠር መቻሉን ማስታወቁ ይታወሳል።