በኢትዮጵያ መንግስትና በህወሓት ድርደር አሜሪካ፣ ተመድና ኢጋድ በታዛቢነት እየተሳተፉ ነው- አፍሪከ ህብረት
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል ድርድር መይፋ መጀመሩን የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል
ድርድሩን ኦሊሴንጎን ኦባሳንጆ እና ኡሁሩ ኬንያታ እንደሚመሩት አፍሪከ ህብረት ገልጿል
በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የሚደረገው ድርድር በይፋ መጀመሩን የአፍሪካ ህበረት አስታወቀ።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት ማሻውን ባወጡት መግለጫ በኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል የሚደረገው የመጀመሪያው የፊት ለፊት የሰላም ንግግር መጀመሩን አብስረዋል።
የሰላም ንግግግሩን የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልእከተኛ የሆኑት የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ፣ የኬንያ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የደቡብ አፍሪካ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ፉምዚል ማላምቦ ናግኩዋ እየመሩት መሆኑንም የአፍሪካ ህብረት አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ)፣ የአሜሪካ መንግስት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ድርጅት (ኢጋድ) ተወካዮች “በታዛቢነት” እየተሳተፉ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ደቡብ አፍሪካ የሰላም ድርድሩን ለማስተናገድ ፍቃደኛ በመሆኗ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት ሀገሪቱን እና ፕሬዝዳን ሲሪል ራማፖሳን አመሰግነዋል።
ሙሳ ፋኪ ማህማት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ሰላምን ለማስፈን ባሳዩት ቁርጠኝነት ይበልጥ እንደተበረታቱም አስታውቀዋል።
በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው የሰላም ድርድር ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከሁለት ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄድ መደበኛ ንግግር ነው።
በአፍሪካ ህብረትአሸማጋይነት በሚካሄደው ድርድር ላይ በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት በትናትናው እለት ተደራዳሪዎቻቸውን ወደ ደቡብ አፍሪካ መላካቸውን መግለጻውን ይታወሳል።
በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚስቴር እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደመቀ መኮንን የተደራዳሪውን ቡድን እንዲመሩ መሰየማቸውን መንግሰት ማስታወቁ ይታወሳል።
ቀደም ሲል ህወሓት በአፍሪካ ህብረት ስር ለመደራደር ፍቃደኛ መሆኑን በገለጸበት መግለጫው ቡድኑ የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳን እና ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤን እንደሚያካትት መግለጹ ይታወሳል።