በዩክሬን ጉዳይ ሲወያዩ የነበሩት ሩሲያና እና አሜሪካ መግባባት አልቻሉም ተባለ
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜንዲ ሸርማን “እኛ ጠንካራ አቋም አለን… የደህንነት ሀሳባችን እንዲፈጸም ግፊተችንን እንቀጥላለን፡፡”
ሩሲያ፣ ዩክሬን በፍጹም የኔቶ ጦር አባል እንዳትሆን ማረጋገጥ “ግዴታ” ነው ብላለች
በዩክሬን ጉዳይ በጄኔቫ ሲወያዩ የነበሩት ሩሲያ እና አሜሪካ በመካከላቸው የነበረውን ልዩነት ስለማጥበባቸው ያሳዩት ምልክት የለም፡፡
ሩሲያ በዩክሬን ድንበር ወታደሮች ማከማቸቷንና በአሜሪካ የሚመራው የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን ድርጅት(ኔቶ) ወደ ቀድሞ የሶቪት ግዛት መጠጋቱን እንዲያቆም መጠየቋን ቀጥላለች፡፡
“እንዳለመታደል ሆኖ በዚህ ጉዳይ ከፍተኛ ልዩነት ያለው አተያይ አለን፡፡ አሜሪካና እና ሩሲያ ምን መሰራት አለበት በሚለው ጉዳይ ላይ ተቃራኒ የሆነ መንገድ ነው የሚከተሉት” ሲሉ የሩሲያው ምክትል የውጭ ጉዳይ ሰርጌ ራያብኮቭ ተናግረዋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜንዲ ሸርማን “እኛ ጠንካራ አቋም አለን… የደህንነት ሀሳባችን እንዲፈጸም ግፊተችንን እንቀጥላለን፡፡”
አሜሪካ እና ዩክሬን እንዳሉት ሩሲያ ክሪሚያን ከያዘች ከ8 አመታት በኋላ 100ሺ የሩሲያ ወታደሮችን ለማጥቃት በሚያስችል ርቀት ላይ ያሰፈረችው ምናልባትም ለአዲስ ወረራ ለመዘጋጀት ሊሆን ይችላል ብለዋል፡፡
ሩሲያ በአንጻሩ እንዲህ አይነት እቅድ አስተባብላለች፤ አደገኛ ለሆነው የኔቶ እንቅስቃሴ መልስ የመስጠት ጉዳይ መሆኑን ገልጻለች፡፡
ራያብኮቨ የነቶ ጦር መስፋፋት እንዲቆምና በማእከላዊና በምስራቅ አውሮፓ የጥምር እንቅስቃሴ እንዲቆም ጠይቃለች፡፡
ምክትል ሚኒስትሩ እንዳሉት ዩክሬን በፍጹም የኔቶ አባል እንዳትሆን ማረጋገጥ ግዴታ ነው ብለዋል፡፡ ነገርግን አሜሪካ በሩሲያ ሀሳብ አትስማማም፡፡