የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ባንኮች ላይ የተጣለውን ማዕቀብ መሻሻያ እንደሚያደረግ አስታወቀ
ህብረቱ ማሻሻያውን ለማድረግ የሚያስችለውን “ረቂቅ ሰነድ” ረቡዕ እለት ያጸድቃል ተብሎም ይጠበቃል
አውሮፓ ህብረት ሩሲያ የምግብ አቅርቦትን እንደ ‘ድብቅ ሚሳኤል’ እየተጠቀመችበት ነው የሚል ክስ ያቀርባል
የአውሮፓ ህብረት በዓለም አቀፍ የምግብ እና ማዳበሪያ ንግድ ላይ ያሉ ማነቆዎችን ለማቃለል በሞስኮ ባንኮች ላይ የጣለውን ማዕቀብ እንደሚያሻሽል አስታወቀ፡፡
ህብረቱ ማሻሻያወን ለማድረግ በሚያስችለው ረቂቅ ሰነድ ላይ በመምከረም ተሰምቷል፡፡
ህብረቱ በሩሲያ ባንኮች ላይ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ የዓለም የምግብ አቅርቦት ላይ ከፍተኛ ችግር መፈጠሩ አይዘነጋም፡፡
በተለይም ሩሲያ በጥቁር ባህር የሚገኙ ወደቦች ዝግ ማድረጓ፤ የምግብ እጥረቱ በተለይም እንደ አፍሪካ ባሉ ክፍለ አህጉራት ከፍተኛ ጫና መፍጠሩ የአፍሪካ ህብረትም ጭምር ሲገልጽ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡
እናም ችግሩን ከግምት ያስገባው የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ የገንዘብ ተቋማት ላይ በጣለው ማዕቀብ ላይ ማሻሻያ አደርጋለሁ ብሏል፡፡
አንድ የአወሮፓ ህብረት ለሮይተርስ እንደተናገሩት ከሆነ፤ ረቂቅ ሰነዱ ረቡዕ የሚጸድቅ ይሆናል፡፡
አውሮፓ ህብረት ሩሲያ የምግብ አቅርቦትን እንደ ‘ድብቅ ሚሳኤል’ እየተጠቀመችበት ነው የሚል ክስ ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚሸል ከአንድ ወር በፊት በኒውዮርክ በነበረው የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ስብሰባ እንደተናገሩት፤ ሩሲያ የምግብ አቅርቦትን እንድ ድብቅ ሚሳዔል በመጠቀም በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራትን ለከፋ ድህነት እየዳረገች ነው ሲሉ ከሰዋል፡፡
ሚሸል “የሚያሳዝነው ሩሲያ የጀመረችው ጦርነት በመላው ዓለም እየተዛመተ መሆኑ ነው፤ የምግብ ዋጋ እጅጉን እንዲንር በማድረግ የዓለም ህዝቦች ለድህነት እንዲዳረጉና የተለያዩ ቀጠናዎች እንዲታመሱ እያደረገ ነው ፤ለዚህ ሁሉ ቀውስ ተጠያቂ ሩሲያ መሆኗ ሊታወቅ ይገባል” ነበር ያሉት፡፡
ሩሲያ ግን በተወካይዋ አማካኝነት “መሰረተ ቢስ” ስትል በወቅቱ ክሱን ውድቅ ማድረጓ ይታወቃል፡፡