ፖለቲካ
ኢራን በአንድ ጊዜ ሶስት ሳተላይቶችን አስወነጨፈች
ቴክኖሎጂውን የረጅም ርቀት ሚሳይል ለማስወንጨፍ ጥቅም ላይ ልታውለው ትችላለች በሚል አውሮፖውያን ሰግተዋል
ኢራን አውሮፖውያን ሳተላይት ማስወንጨፏን ተከትሎ ያቀረቡትን ውግዘት አጣጥላለች
ኢራን በአንድ ጊዜ ሶስት ሳተላይቶችን አስወነጨፈች።
ኢራን በመከላላከያ ሚኒስትር በበለጸገው የሲሞሟርግ ሳተላይት ተሸካመሚ ሮኬት በመጠቀም ለመጀመሪያ ጊዜ በተመሳሳይ ሰአት ሶስት ሰተላይቶች በዛሬው እለለት አስወንጭፋለቸች።
አንዱ ሳተላይት 32 ኪሎ ግራም እንደሚመዝን እና ሁለት ደግሞ እየያንዳንዳቸው 10ኪሎግራም የሚመዝኑ መሆናቸውን ሮይተርስ የኢራን ሚዲያዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።
እንደዘገባው ከሆነ ሁለቱ ትናንሽ ሳተላይቶቹ 'የናሮውባንድ' ግንኙነት እና ጂኦፖዚሽኒንግ ለመሞከር ጥቅም ላይ ይውላሉ።
በኢራን ስፔስ ኤደንሲ የተሰራቸችው"ማህዳ" የተሰኘችው ትልቋ ሳተላይት የሲምሮግ ሮኬትን ትክክለኛነት ለመሞከር ነው ተብሏል።
ኢራን በኢሊት ሪቮሉሽናሪ ጋርድ በተሰራ ሮኬት ሶራያ ሳተላይት ወደ ኦርቢት ማምጠቅ መቻሏ፣ ቴክኖሎጂውን የረጅም ርቀት ሚሳይል ለማስወንጨፍ ጥቅም ላይ ልታውለው ትችላለች በሚል አውሮፖውያን ሰግተዋል።
ኢራን አውሮፖውያን ሳተላይት ማስወንጨፏን ተከትሎ ያቀረቡትን ውግዘት አጣጥላለች።