የብሊንከን ጉብኝት “በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ቀውስና በአየረንብረት ለውጥ” ጉዳይ ያተኩራል ተብሏል
ሶስት የአፍሪካ ሀገራትን ለመጎብኘት በትናንትናው እለት ጉዞ የጀመሩት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን በዛሬው እለት ኬንያ ደርሰዋል፡፡
አንቶኒዮ ብሊከን እስከ ቅዳሜ ድረስ፤ በጆባይደን ለሚመራው የአሜሪካ አስተዳደር ቁልፍ አጋር ናቸው የተባሉትን ናይጀሪያንና ሴኔጋልን ይጎበኛሉ ተብሏል፡፡
የአየርንብት ለውጥና በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ቀውስ የብሊንከን የጉብኝት ትኩረት እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ በምጣኔ ሃብታዊ፣ በአየር ንብረት እና በዴሞክራሲያዊ እንዲሁም በጸጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ ከሚጎበኗቸው ሃገራት መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ ተናግረዋል፡፡
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ብሊንከን ወደ አፍሪካ ጎዞ እንደሚደርጉ ካሳወቁ በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር መገናኘታቸው ይታወሳል፡፡ ፕሬዝዳንት ኬንያታ ወደ አዲስ አበባ የመጡበት ጉዳይ ግን ግልጽ አልተደረገም፡፡
ፕሬዝዳንቱ ከአሁን ቀደም፤ በተለይም ወደ አሜሪካ አቅንተው በዋሽንግተን ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ተወያይተው ከተመለሱ በኋላ የኢትዮጵያ ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁመው ወደ ድርድር እንዲመጡ ሲያሳስቡ እንደነበር ይታወሳል፡፡
አሜሪካም በኢትዮጵያ ያለው ግጭት ቆሞ፣ ሰላማዊ መፍትሄ ይፈለግ የሚል አቋም በተደጋጋሚ እያንጸባረቀች ትገኛለች፡፡
በፌደራል መንግስትና በህወሓት መካከል የነበረው አለመግባባት ወደ ወታራዊ ግጭት ያመራው፤ ጥቅምት 24፣2013ዓ.ም ህወሓት በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ ነበር፡፡
መንግስት ክህደት ፈጽሟል ባለው ህወሓት ላይ “የህግ ማስከበር ዘመቻ” በማወጅ የትግራይ ዋና ከተማና ብዙ ቦታዎችን መያዝ የቻለው መንግስት ከ8 ወራት በኋላ ለትግራይ ህዝብ የጽሞና ግዜ ለመስጠት በማሰብ ከትግራይ ክልል ሰራዊቱን ማስወጣቱ ይታወሳል። በክልሉ በነበረው ጦርነት ወቅት ዜጎች መፈናቃላቸውንና መገደላቸውን ኢሰመኮና ሌሎች አለምአቀፍ ተቋማት መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
መንግስት ጦሩን ከክልሉ ማስወጣቱን ተከትሎ፣ ሕወሓት ወደ አማራ አፋር ክልል በመግባት ጥቃት በመሰንዘር፤ ሰዎች እንዲገደሉና በ2 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን የክልሉ መንገስት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
አሁን ጦርነት ባለባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ህዝብ ለርሃብና ለሞት አደጋ የተዳረገ ተዳርገዋል ብሏል ክልሉ፡፡
መንግስት በኢትዮጵያ በሽብር የተፈረጀው ህወሓት ደቅኖታል ያለውን ሉአላዊነትን ችግር ውስጥ የሚያስገባ አደጋ ለመቀልበስ ባለፈው ሳምንት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል።
በአፍካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ኦሊሰጉን ኦባሳንጆ፣ በኢትዮጵያ አንድ አመት ያስቆጠረውን ግጭት በሰላማዊ መንገድ እየተንቀሳቀሱ መሆናቸውን መግለጻቸው ይታወሳል፡፡