መኪናው ከትራንስፖርት ባለፈ የመዋኛ፣ አነስተኛ የጎልፍ ሜዳ እና አነስተኛ ሂልኮፕተር ማረፊያ ቦታ አለው ተብሏል
በ26 ጎማዎች የሚንቀሳቀሰው የዓለማችን ረጅሙ መኪና
በፈረንጆቹ 1986 18 ሜትር የሚረዝመው መኪና ላለፉት 40 ዓመታት የዓለማችን ረጅሙ መኪና ተብሎ በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ሰፍሮ ቆይቷል፡፡
አሁን ደግሞ የአሜሪካ ህልም ስያሜ የተሰጠው እና በ26 ጎማዎች የሚንቀሳቀስ አንድ አስገራሚ መኪና መሰራቱን ተገልጿል፡፡
መኪናው ሚካኤል ዴዘር እና ሚካኤል ማኒንግ የተሰኙ ሁለት አሜሪካዊያን እንደተሰራ የተገለጸ ሲሆን ባንድ ጊዜ 75 አዋቂዎችን መጫን የሚችል ነው፡፡
ይህ መኪና በኒው ጀርሲ ለዓመታ ቆሞ የነበረ መኪናን በመግዛት እና የተለያዩ ጥገናዎች እንደተደረጉለት ባለቤቶቹ ተናግረዋል፡፡
መኪናው የአሁኑን መልክ እስኪይዝ ዓመታትን የፈጀ ጥገና ተደርጎለታል የተባለ ሲሆን በመጨረሻም ለእይታ እንደበቃ የድንቃ ድንቅ መዝገብ በድረገጹ ይፋ አድርጓል፡፡
ለመንዳት ይከብዳል የተባለው ይህ የዓለማችን ረጅሙ መኪና 30 ነጥብ 5 ሜትር ርዝመት እንዳለው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
መኪናው አልጋ፣ የመዋኛ ገንዳ፣ ቅንጡ መታጠቢያ፣ አነስተኛ የጎልፍ ሜዳ እና አነስተኛ የሂልኮፕተር ማረፊያ አለውም ተብሏል፡፡
በኦረላንዶ የመኪና ሙዚየም ውስጥ የጠቀመጠው ይህ መኪና ባንድ ጊዜ 75 አዋቂ ሰዎችን ዘና አድርጎ ያጓጉዛል የተባለ ሲሆን መኪናው ቀጥ ባሉ መንገዶች ላይ ብቻ እንደሚነዳ ተገልጿል፡፡