ፖለቲካ
አሜሪካ፤ ቱርክ የስዊድን የኔቶ አባል መሆን ጥያቄ በአፋጣኝ እንድታጸድቅ አሳሰበች
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ማኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ቱርክ የስዊድንን ኔቶን የመቀላቀል ጥያቄ በአፋጣኝ እንድታጸድቅ አሳስበዋል
"ብሊንከን ጊዜው አሁን ነው፤ ላለመፍጠን ምንም ምክንያት የለም ብለዋል"ብሊንከን
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ማኒስትር አንቶኒዮ ብሊንከን ቱርክ የስዊድንን ኔቶን የመቀላቀል ጥያቄ በአፋጣኝ እንድታጸድቅ አሳስበዋል።
ሚኒስትሩ የኖርዲክ ሀገራት የቱርክን ተቃውሞ በመረዳት አስፈላጊውን እርምጃ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
ብሊንከን የባይደን አስተዳደር የቱርክን ስዊድንን የኔቶ አባል አድርጋ የማጽደቅ ጉዳይ ለአንካራ ከሚደረገው የኤፍ-16 አውሮፕላን ሽያጭ ጋራ ይያያዛል የሚለውን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል።
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ፕሬዝደንት ባይደን ጉዳዩ ግንኙነት እንዳለው ከገለጹ ከአንድ ቀን በፊት ነው።
ብሊንከን ከስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በመሆን በስዊድን በጋራ በሰጡት መግለጫ ስዊድን ከሔምሌ አጋማሽ በፊት ከሚዲረገው የኔቶ ስብሰባ በፊት አባልነቷ እንዲጸድቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
"ብሊንከን ጊዜው አሁን ነው፤ ላለመፍጠን ምንም ምክንያት የለም ብለዋል"ብሊንከን።
ብሊንከን ቱርክ ተገቢ የሆኑ ስጋቶችን ማንሳቷን እና እነዚህን ስጋቶች ፊላንድ እና ስዊድን መቅረፋቸውን ቸናግረዋል።
ስዊድን የኔቶ አባል የማድረጉ ሂደት በመጭዎቹ ሳምንታት የፈጸማል ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።