አሜሪካ "የኮፕ 28 ስኬት በሚቀጥሉት ዓመታት ለትላልቅ የአየር ንብረት ውሳኔዎች መንገድ ይከፍታል" አለች
የአሜሪካ የአየር ንብረት ጉዳይ ልዩ ተወካይ ጆን ኬሪ ከአረብ ኤሚሬትስ ጋር በቅርበት እየሰሩ መሆኑ ተገለጸ
ኮፕ-28 በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በዱባይ ኤክስፖ ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2023 ይካሄዳል
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አረብ ኢሚሬትስ የምታዘጋጀው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-28) ስኬት በሚቀጥሉት ዓመታት ለትልቅ የአየር ንብረት ውሳኔዎች መንገድ ይከፍታል ብላ እንደመትማን አስታወቀች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በተለይ ለአል ዐይን ኒውስ በሰጡት መግለጫ፤ የኮፕ 28 ስኬታማነት ለማረጋገጥ የአሜሪካ የአየር ንብረት ጉዳይ ልዩ ተወካይ ጆን ኬሪ ከአረብ ኤሚሬትስ ጋር በቅርበት እየሰሩ ነው ብሏል።
- የአየር ንብረት ፋይናንስ ጉዳይን መፍታት በኮፕ28 ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው- ዶ/ር ሱልጣን አልጃበር
- ኮፕ28 ጉባዔ በአየር ንብረት ዙሪያ ያለውን አረዳድ የሚቀይር ነው- ተመድ
አረብ ኢሚሬትስ የምታዘጋጀው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ-28) በሚቀጥሉት አመታት ለበለጠ የአየር ንብረት ግቦች መንገድ የሚከፍት የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ መድረክ እንደሚሆንም አሜሪካእምነቷን ገልጻለች።
ኮፕ28 የፓሪስ ስምምነት ግቦችን ለማሳካት የተደረገውን ዓለም አቀፍ ስራ ይገግማል ያሉት ቃል አቀባዩ፤ ይህ ግምገማ በአየር ንብረት ድርድር ታሪክ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ይካሄዳል ብለዋል።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ በአረብ ኤምሬትስ በሚካሄደው ኮንፈረንስ ሁሉም ተሳታፊዎች ባለፉት አስርት አመታት የዓለም ሙቀትን ወደ 1.5 ከ1.5 ዲግሪ ሴልሺየስ ለማውረድ በወሰዷቸው እርምጃዎች ዙሪያ ታዓማኒነት ያላቸውን ማስረጃዎች ይዘው እንዲቀርቡ አሳስበዋል።
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የአየር ንብረት ጉዳይ ልዩ ተወካይ ጆን ኬሪ አረብ ኤሚሬትስ ነዳጅ አምራች ከሆኑ ሀገራት መካከል የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት የምታደርገው ጥረት የተለየ መሆኑን አረጋግጠዋል።
ጆን ኬሪ ኮፕ28 ኮንፈረንስ ስኬታማ እንዲሆን አረብ ኤሚሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያንን እና የኮፕ-28 ፕሬዝዳንትና የአረብ ኢሚሬትስ የኢንዱስትሪ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር ሱልጣን አል ጃበር እየሰሩት ላለው ስራ አመስግነዋል።