ኮፕ28 ጉባዔ በአየር ንብረት ዙሪያ ያለውን አረዳድ የሚቀይር ነው- ተመድ
በአረብ ኤምሬትስ የሚካሄደው ኮፕ 28 የፓሪሱን ስምምነት ግቦችን ለማሳካት እርምጃ የሚወደስበት እንደሚሆን ተስፋ ተጥሎበታል
የአየር ንብረት ለውጥ ኮንቬንሽን ዋና ዳይሬክተር ሲሞን ስቲል ኮፕ28 የአየር ለውጥ እርማጀዎች አካሄድን የሚያስተካክል ይሆናል ብለዋል
ኮፕ28 ጉባዔ በአየር ንብረት ዙሪያ ያለውን አረዳድ እና አካሄድን የሚያስተካከል እንደሚሆን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ስምምነት ዋና ዳይሬክተር አስታወቁ።
የተመድ የአየር ንብረት ስምምነት ዋና ዳይሬክተር ሲሞን ስቲል ለአል ዐይን ኒውስ እንደተናገሩት ኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ እርምጃዎች አካሄድን የሚያስተካክል እንደሚሆነ ጠቁመዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ ባለፈው ዓመት መጨረሻ በግብፅ የተካሄደው ኮፕ27 ጉባዔ በታዳጊ ሀገራት ለደረሰው ኪሳራ እና ኪሳራ ማካካሻ ፈንድ ለማቋቋም መወሰኑን ጠቁመዋል።
ይህም በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት እርምጃ ውስጥ ካሉት ታሪካዊ ውሳኔዎች አንዱ እንደሆነም ጠቁመዋል።
ሲሞን ስቲል በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ የሚካሄደ የአየር ንብረት ለውጥ ኮንፈረንስ (ኮፕ28) የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት እርምጃ የሚወሰድብት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል።
በአረብ ኤምሬትስ የሚካሄደው ኮፕ28 ኮንፈረንስ ባለፈው ዓመት በግብፅ ሻርም ኤል ሼክ ሲካሄድ የቆየው ኮፕ27 ቀጥሎ የሚካሄድ ሁለተኛው ጉባኤ ነው።
የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ዋና ዳይሬክተሩ ኮፕ28 ጉባኤ በዓለም ላይ ከፍተኛ ነዳጅ አምራች ከሆኑት አካባቢዎች አንዷ በሆነችው አረብ ኤምሬትስ መካሄዱ ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለውም ተናግረዋል።
በ2015 የፓሪስ ስምምነት ግቦች መሰረት የዓለም ሙቀት መጨመርን ወደ ቅድመ-ኢንዱስትሪ ደረጃዎች በመመለስ የ1.5 ዲግሪ ሴንቲግሬት የማውረድ ግብ ማስጠበቅ የኮፕ28 ዋና ዋና ጉዳዮች መካከል አንዱ እንደሆነ ይጠበቃል።