የቦይንግ ኩባንያ 25 ቢሊዮን ዶላር እንዲቀጣ የአደጋው ሰለባዎች ቤተሰቦች ጠየቁ
ሁለቱም አደጋዎች በበረራ መቆጣጠሪያ ስርአት ብልሽት ምክንያት ነበር የተከሰቱት።
በፈረንጆቹ በ2018 እና በ2019 በደረሱ ሁለት የመከስከሰ አደጋዎች 346 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል
የቦይንግ ኩባንያ 25 ቢሊዮን ዶላር እንዲቀጣ የአደጋው ሰለባዎች ቤተሰቦች መጠየቃቸው ተገለጸ።
በሁለት የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖች አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ሰለባዎች ቤተሰቦች "በአሜሪካ ታሪክ ከባድ ለተባለው ኮርፖሬት ክራይም" 24.8 ቢሊዮን ቅጣት እንዲጣል እና ክስ እንዲመሰረት መጠየቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
ቦይንግ በፈጸመው ወንጀል የደረሰው የሞት መጠን ከባድ በመሆኑ መጠኑ "ምክንያታዊ እና ተገቢ ነው" ብሏል የቤተሰቦቹ ጠበቃ ፓውል ካሴል።
ቢቢሲ እንደገለጸው ካሴል ባቀረበው ባለ 32 ገጽ ደብዳቤ በ2018 እና በ2019 በደረሱ ሁለት የመከስከሰ አደጋዎች 346 ሰዎች በሞቱበት ወቅት ኩባንያውን ሲመሩ የነበሩ ሰዎች መከሰሰ አለባቸው ብሏል።
ይህ ደብዳቤ የቦይንግ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዴቭ ካልሆን ባለፈው ማክሰኞ እለት በኮንግረስ ፊት ቀርበው ይቅርታ መጠየቃቸውን ጠቅሷል።
"ላደረስነው ገዳት ይቅርታ እጠይቃለሁ" ሲሉ የሰለባዎቹ ቤተሰቦች በጩኸት ንግግራቸውን አቋርጠዋቸዋል ተብሏል።
ሁለቱ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ የደረሰባቸው በተለያየ ጊዜ ቢሆንም የአደጋው መንሰኤ ግን ተመሳሳይ ነበር።
በፈረንጆቹ ጥር 2018 ንብረትነቱ የላዮን ኤየር ፍላይት የሆነ አውሮፕላን ከኢንዶንኤዥያ ዋና ከተማ ጃከርታ ከተነሳ ከ13 ደቂቃ በኋላ ባጋጠ መው የመከስከሰ አደጋ ተሳፍረው የነበሩ 189 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
በመጋቢት 2019 ደግሞ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየርመንገድ የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከቦሌ አለምአቀፍ አየር ማረፊያ ከተነሳ ከስድስት ደቂቃ በኋላ ሲከሰከሰ አሳፍሯቸው የነበሩት 157 ሰዎች ሞተዋል። በሁለቱም አደጋዎች በህይወት የተረፈ ሰው የለም።
ሁለቱም አደጋዎች በበረራ መቆጣጠሪያ ስርአት ብልሽት ምክንያት ነበር የተከሰቱት።
ኮልሆን ኮንግረስ በቀረቡበት ወቅት ኩባንያው ስህተት መስራቱን አምነው እና ከስተቱ ተምሯል ብለዋል።
ዋና ስራ አስፈጻሚው ቦይንግን ሚስጥር በማያወጡ ግለሰቦች ላይ እርምጃ መውሰዱን ገልጾ፣ የስራተኞቹን ስጋት ግን እንደሚያዳምጥ ተናግረዋል። የአሜሪካ የፍትህ ክፍል ወይም ጀስቲሰ ዲፓርትመን ከሁለት የመከስከስ አደጋዎች ጋር በተያያዘ በቦይነረግ ላይ በፈረንጆች 2021ጀምሮት የነበረውን የወንጀል ክስ እንደገና ለመጀመር እያጤነው ነው።
ክስ የቆመው ኩባንያው የአየር ተቆጣጣራዎችን ማሳሳቱን ካመነ እና ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች የሚቆጣጠር አዲስ ኮምፒሊያንስ ስርአት ለመዘርጋት ቃል መግባቱን ተከትሎ ነበር።
ባለፈው ወር በረራ ላይ የነበረ 737 ማክስ አውሮፕላን በሩ ከተገነጠለ በኋላ አቃቤ ህግ ቦይንግ ስምምነቱን ጥሷል የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል።
ጀስቲስ ዲፓርትመንት እስከ ፈረንጆቹ ሐምል ሰባት ድረስ ክሱ እንደገና ይጀመር ወይስ አይጀመር በሚለው ጉዳይ ውሳኔ ይሰጣል።
ካሴል ደንበኞቻቸው ወይም የአደጋ ሰለባ ቤተሰቦች በቦይንግ ላይ ወደፊት ከሚጣለው ቅጣት ላይ የተወሰነው የኩባንያውን ደህንነት እና የጥንቃቄ አሰራሮች የሚቆጣጠር ነጻ ተቆጣጣሪ ለማቋቋም እንዲውል ሀሳብ ማቅረባቸውን ገልጸዋል።