የቦይንግ ምርት የሆነው 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ላይ እክል ከገጠመው ጀምሮ ተደጋጋሚ የጥራት ችግሮች እየታዩበት ገኛሉ
ቦይንግ ኩባንያ ተጨማሪ የምርት ጉድለቶች ተገኙበት፡፡
የዓለማችን ግዙፍ የአቪየሽን ኩባንያ የሆነው ቦይንግ ካሳለፍነው ጥር ወር ጀምሮ በ737 ማክስ 9 አውሮፕላን መስኮቱ ተገንጥሎ መውደቁን ተከትሎ ትችቶችን እያስተናገደ ይገኛል፡፡
ከዚህ ጊዜ በኋላ ተደጋጋሚ የምርት ጥራት ችግሮች የተከሰቱ ሲሆን የአሜሪካ አቪዬሽን አስተዳድር በኩባንያው ላይ የቴክኒክ ጥራት ምርመራዎችን አድርጓል፡፡
ኩባንያው በቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን ምርቶች ላይ ካከናወናቸው 89 የጥራት ምርመራዎች ላይ በ33ቱ ጉድለት እንደተገኘበት ኒዮርክ ታየምስ ዘግቧል፡፡
ይህ አውሮፕላን በተለይም የኤሮ ሲስተሙ ሲፈተሸ የጥራት ደረጃውን ያሟላው ከ13 ነጥቦች በስድስቱ ብቻ አልፏል ተብሏል፡፡
የኩባንያው የቴክኒክ ባለሙያዎች ስለ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በቂ እውቀት እንዳላቸው በተደረገው ምርመራ የሚገባውን ያህል ያውቃሉ የሚለውን ኩባንያው ማስረዳት እንዳልቻለም ተገልጿል፡፡
የቦይንግ ኩባንያ ሚስጢሮችን ያጋለጠው ሰው ሞቶ ተገኘ
ቦይንግ በበኩሉ የአሜሪካ አቪዬሽን አስተዳድር ባስቀመጠው ጥራት ደረጃዎች መሰረት መተግበር መጀመሩን አስታውቋል፡፡
የአሜሪካ አቪዬሽን ባለስልጣንም ቦይንግ ኩባንያ 737 ማክስ 9 አውሮፕላንን እንዳያመርት፣ የተስተዋለበትንም የጥራት ችግር በሶት ወራት ውስጥ እንዲፈታ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል፡፡
ቦይንግ በበኩሉ የ737 ማክስ 9 አውሮፕላን ምርት ሀላፊን ከሀላፊነት ያነሳ ሲሆን በ90 ቀናት ውስጥ የተከሰቱ የጥራት ችግሮችን እንደሚፈታ አስታውቋል፡፡