በረራ ላይ ሳለ 'ፓኔል' የጠፋበት የቦይንግ አውሮፕላን ምርመራ እየተካሄደበት ነው ተባለ
የፓኔሉ መጥፋት የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ካጋጠሙት ክስተቶች ውስጥ የቅርብ ጊዜው ነው
የአሜሪካ የፌደራል አቬሽን ባለስልጣን ንብረትነቱ የዩናይትድ ኤርላይንስ የሆነው ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን ፓኔሉ እንዴት እንደጠፋበት እየመረመረ ይገኛል
በረራ ላይ ሳለ 'ፓኔል' የጠፋበት የቦይንግ አውሮፕላን ምርመራ እየተካሄደበት ነው ተባለ።
የአሜሪካ የፌደራል አቬሽን ባለስልጣን(ኤፍኤኤ) ንብረትነቱ የዩናይትድ ኤርላይንስ የሆነው ቦይንግ 737-800 አውሮፕላን በአሜሪካ ኦሪጎን በሰላም ከማረፉ በፊት ኤክስተርናል ፓኔሉ እንዴት እንደጠፋበት እየመረመረ ይገኛል።
የፓኔሉ መጥፋት የአውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ካጋጠሙት ክስተቶች ውስጥ የቅርብ ጊዜው ነው።
የበረራ ቁጥሩ 433 የሆነው ይህ አውሮፕላን ከሳንፍራንሲስኮ ተነስቶ በኦሪጎን በሚገኘው ሮጉ ቫሊ አለምአቀፍ አየር መንገድ ማረፉን የገለጸው ኤፍኤኤ ካረፈ በኋላ በተደረገ ምርመራ የጠፋ ፓኔል መኖሩ ተረጋግጧል ብሏል።
አውሮፕላኑ የተነሳበት ሜዴፎርድ አየር መንገድ ስራ እንዲያቆም ተደርጎ የፓኔሉ ስብርባሪ ቢፈለግም እንዳልተገኘ የአየር መንገዱ ዳይሬክተር አምበር ጁድ ተናግረዋል።
ዩናይትድ እንዳለው ይህ የጠፋው ፓኔል በአውሮፕላኑ በታች በኩል ክንፉ ከዋናው አካል ጋር የሚገናኝበት ቦታ ላይ ያለ እና ከላንዲንግ ጊር(ከማኮብኮቢያ ጎማው) ቀጥሎ ያለ ነው።
25 አመታትን ያስቆጠረው አውሮፕላን 139 ሰዎችን እና ስድስት የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ነበር ተብሏል።
ንብረትነቱ የአላስካ አየርመንገድ የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በረራ ላይ እያለ የአደጋ ጊዜ መውጫ በሩ ተገንጥሎ ከወደቀበት ከባለፈው ጥር ወዲህ ቦይንግ ጥብቅ ምርመራ እየተደረገበት ይገበት ይገኛል።
ክስተቱ አብራሪዎቹ አውሮፕላኑን በድንገት እንዲያሳርፉት አስገድዷቸው ነበር።
174 መንገደኞችን እና ስድስት አስተናጋጆች አሳፍሮ የነበረው በድንገት በሚያርፍበት ወቅት በተወሰኑ መንገደኞች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።
የአሜሪካ ተቆጣጣሪዎች ኩባንያው በምርት ሂደት በሚከተላቸው የጥንቃቄ እና የጥራት ደረጃዎች ላይ ወዲያውኑ ነበር ምርመራ የከፈቱት። ኤፍኤኤ በምርመራው በቦይንግ ውስጥ በምርት ሂደት ደረጃቸውን ያልጠበቁ አሰራሮች መኖራቸውን ገልጾ፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ 171 ማክስ 9 አውሮፕላኖች ሰራ እንዲያቆሙ አዞ ነበር። ከዚህ በተጨማሪም የአሜሪካ የናሽናል ትራንስፖርቴሽን ሴፍቲ ቦርድ በቦይንግ ላይ ሌላ ምርመራ እንዲደረግበት ከፍቷል።
የዩናይትድ አየር መንገድ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት አውርፕላኑ በበረራ ላይ እያለ ጉዳት ስለመኖሩ የሚያመለክት ነገር ባለመኖሩ የአደጋ ጊዜ እርምጃዎች አልተወሰዱም ብለዋል።
"አውሮፕላኑ በድጋሚ ወደ ስራ ከመመለሱ በፊት አስፈላጊውን ጥገና እና ምርመራ እናደርጋለን" ብሏል አየርመንገዱ።
ቦይንግ በአላስካ አየርመንገድ ያጋጠመውን ክስተት ተከትሎ የአመራር ለውጥ ቢያደርግም የገበያ ድርሻለው ከተወናቃኙ አየርባስ ጋር ሲነጻጸር ዝቅ ብሎበታል።