የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ እጃቸውን ለፖሊስ ሰጡ
ዙማ መረጃ ለመስጠት ባለመተባበራቸው ለፍርድቤት ንቀት አሳይተዋል በሚል የ15 ወራት እስር ተላልፎባቸዋል
ጃኮብ ዙማ በስልጣን ዘመናቸው የሙስና ወንጀልን ፈጽመዋል በሚሉ ተደራራቢ ወንጀሎች መከሰሳቸው የሚታወስ ነው
የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ለፖሊስ እጅ መስጠታቸው ተሰምቷል።
ለፍርድ ቤቱን ንቀት አሳይተዋል በሚል የ15 ወራት እስር የተፈረደባቸው ዙማ እጄን ለፖሊስ እጅ አልሰጥም ሲሉ መቆታቸው ይታወቃል።
ጃኮብ ዙማ በህግ ቁጥጥር ስር የሚውሉበት ቀን እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመኖሪያ ቤታቸው ዙሪያ ለተሳበሰቡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው መብታቸው መጣሱን መናገራው ይታወሳል።
ፖሊስ ፕሬዝዳንቱ እጃቸውን ለፖሊስ እንዲሰጡ ቀነ ገደብ አስቀምጦ የነበረ ሲሆን፤ ቀነ ገደቡም ትናነት እኩለ ሌሊት ላይ ነበር የሚጠናቀቀው።
ፕሬዘዳንቱ የሚታሰሩ ከሆነ ደጋፊዎቻቸው በደቡብ አፍሪካ አመጽ እናስነሳለንበማለትም ሲዝቱ ቆይተዋል።
በመጨረሻም ትናት ምሽት ተፈረደባቸውን የእስር ጊዜ ለመጀመር ትናት ምሽት ለፖሊስ እጃቸውን መስጠታቸው ተሰምቷል።
የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ በትናትናው እለት በካዋዙሉ ናታለ ከሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ወስዶ ወደ ማረፊ ቦታ አድርሷቸዋል።
የ79 ዓመቱ ቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ፍርድ ቤት ለሚያደርገው የሙስና ወንጀል ምርመራ መረጃ ለመስጠት ሲጠየቁ በተደጋጋሚ ባለመተባበራቸው፣ ለፍርድ ቤቱን ንቀት አሳይተዋል በሚል የ15 ወራት እስር ተላልፎባቸው ነበር።