ከ87 ዓመት በፊት የተቋቋመው ቮልስዋገን አንድም ጊዜ ፋብሪካውን ዘግቶ አይውቅም
የጀርመኑ ቮልስዋገን ሶስት ፋብሪካዎቹን እንደሚዘጋ አስታወቀ፡፡
በዓለማችን ካሉ ግዙፍ የአውቶሞቲቭ ኩባንያዎች መካከል አንዱ የሆነው ቮልስዋገን ካሉት 10 ፋብሪካዎች ውስጥ ሶስቱን ለመዝጋት መወሰኑን አስታውቋል፡፡
በጀርመን ቀዳሚ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ የሆነችው ጀርምን ኩራት የሆነው ቮልስዋገን ፋብሪካውን ለመዝጋት የወሰነው በትርፍ ማሽቆልቆል ምክንያት ነው ብሏል፡፡
ፋብሪካው ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ በመላው ዓለም ገዢዎች ያሉ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይም ከቻይና እና ከአውሮፓ የነበረውን የገበያ ፍላጎት ቀንሷል፡፡
ይህን ተከትሎም ኩባንያው ኪሳራን ለመነስ በሚል በጀርመን ውስጥ ካሉት 10 ፋብሪካዎች ውስጥ ሶስቱን እዘጋለሁ ያለ ሲሆን በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ሰራተኞቹንም እንደሚያሰናብት ገልጿል፡፡
ጀርመን 250 ሺህ ስራ ፈላጊ ኬንያውያንን ለመቀበል ስምምነት ፈጸመች
ከዚህ በተጨማሪም በቀሪ ሰባት ፋብሪካዎች ውስጥ ለሚቀጥሉት ሰራተኞች የደመወዝ ቅናሽ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
ከሰራተኞች ደመወዝ እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች ዙሪያ ለመምከርም ከሰራተኞች ተወካዮች ጋር የፊታችን ረቡዕ ለመወያት ቀጠሮ መያዙን ዩሮኒውስ ዘግቧል፡፡
ከ87 ዓመት በፊት የተቋቋመው ቮልስዋገን ኩባንያ የማምረቻ ፋብሪካውን ሲዘጋ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡
ቮልስዋገን ኩባንያ በጀርመን ውስጥ ብቻ 300 ሺህ ሰራተኞችን በመቅጠር የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከሚደጉሙት ኩባንያዎች መካከል አንዱ ነው፡፡
ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ ሸማቾች በነዳጅ የሚሰሩ መኪኖችን ከመግዛት ይልቅ በኤሌክትሪክ የሚሰሩትን እየመረጡ ሲሆን ይህ የሽግግር ጊዜም በርካታ ታዋቂ የመኪና አምራች ኩባንያዎችን ገቢ እየጎዳ ይገኛልም ተብሏል፡፡