በአውሮፓ ዋንጫ ምክንያት በጀርመን የከተሙት 100 ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች ከየት የመጡ ናቸው?
ውድድሩ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 14 ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች ወደ ጀርመን ተጉዘዋል ተብሏል
ጀርመን ከ2002 ጀምሮ የወሲብ ንግድን ህጋዊ አድርጋለች
በአውሮፓ ዋንጫ ምክንያት በጀርመን የከተሙት 100 ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች ከየት የመጡ ናቸው?
ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም የተጀመረው የአውሮፓ ወንዶች እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር የፊታችን እሁድ ፍጻሜውን ያገኛል።
በአውሮፓ ግዙፍ ኢኮኖሚ ባላት ጀርመን አስተናጋጅነት እየተካሄደ ያለው ይህ ውድድር ከ እግር ኳሱ ባለፈ ለሆቴሎች እና ሌሎች ንግድ ስራዎች እንዲነቃቁም በር ከፍቷል ተብሏል።
ዩሮ ኒውስ በፍራንክፈርት ያለን አንድ የማህበራዊ ስራዎች ጥናት ጠቅሶ እንደዘገበው እግር ኳስ ውድድሩ ለሴተኛ አዳሪዎችም ሰፊ እድል ፈጥሯል ብሏል።
እንደ ተቋሙ ሪፖርት ከሆነ በጀርመን አሁን ላይ የሴተኛ አዳሪዎች ቁጥር 100 ሺህ ደርሷል።
ከአውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ብቻ 14 ሺህ ሴተኛ አዳሪዎች ወደ ጀርመን ገብተዋል።
በሴተኛ አዳሪነት ስራ የተሰማራች ጃኔ ቫለንቲን እንዳለችው በተለይም በበርሊን ከተማ ደንበኞችን ማግኘት ቀላለ መሆኑን ተናግራለች።
በጀርመን ካሉ አብዛኞቹ ሴተኛ አዳሪዎች ውስጥ ከቡልጋሪያ፣ ሮማኒያ፣ ስሎቫኪያ፣ ቸክ ሪፐብሊክ ፣ፖላንድ እና ሌሎችም ሀገራት የመጡ ናቸው ተብሏል።
በተለይም የአውሮፓ እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ከተጀመረ በኋላ ወደ ጀርመን የገቡት ሴተኛ አዳሪዎች በድህነት ውስጥ የሚኖሩ እንደሆኑም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
የወሲብ ንግድ በጀርመን ከፈረንጆቹ 2002 ጀምሮ ህጋዊ የሆነ ስራ ዘርፍ ሲሆን ከኤችአይቪ ኤድስ እና ከሌሎች የአባላዘር በሽታዎች ነጻ መሆን ግዴታ ካልሆነባቸው ሀገራት መካከልም አንዷ ናት።