“ኮሮና ባስከተለው ችግር መጠን መተባበር አለብን”- የሳኡዲው ንጉስ ሳልማን አብዱላዚዝ
ሳኡዲ አረቢያ ኢኮኖሚዋን ለመቋቋም 11 ትሪሊዮን ወደ ኢኮኖሚው መልቀቋን ንጉሱ ገልጸዋል
የሳኡሲው ንጉስ ሳልማን አብዱላዚዝ የቡድን20 ሀገራት ኮሮና ባስከተለው ችግር መጠን እንዲተባበሩ ጥሪ አቀረቡ
የሳኡሲው ንጉስ ሳልማን አብዱላዚዝ የቡድን20 ሀገራት ኮሮና ባስከተለው ችግር መጠን እንዲተባበሩ ጥሪ አቀረቡ
የሳኡሲው ንጉስ ሳልማን አብዱላዚዝ የቡድን20 አባል ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ባስከተለው ችግር መጠን መተባበር አለባቸው ሲሉ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ንጉሱ ይሄን ያሉት በእሳቸው የሚመራው የቡድን20 ሀገራትን ስብሰባ ባስጀመሩበት ወቅት ነው፡፡
ንጉሱ እንደገለጹት ኮሮና በአለምአቀፍ ደረጃ ከባድ የኢኮኖሚ የማህበራዊ ኪሳራ አድርሷል፤አባል ሀገራቱ ባለፈው ወር ባደረጉት ልዩ የሆነ ስብሰባ ቀውሱን ለመቋቋም 21 ቢሊዮን ዶላር መድበናል ብለዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የአለምን ኢኮኖሚ እንደሚደግፉና ኢኮኖሚዎችና ድንበሮች ተከፍተው የሰዎችንና የንግድ ልውውጥ እንደሚደረግ የተናገሩት ንጉስ ሳልማን ሳኡዲ አረቢያ ኢኮኖሚዋን ለመቋቋም 11 ትሪሊዮን ለግለሰቦችና ለኩባንያዎች መስጠቷን ገልጸዋል፡፡
ንጉስ ሳልማን ለድሃ ሀገራት አግባብ ባለው መልኩ መርዳት እንደሚያስፈልግም ተናግረዋል፡፡
የሪያድ ኢኒሽቲቭ ፎር ግሎባል ትሬድ አለምአቀፍ ችግሮችን እየተቋቋመ ብዙሃን አሳታፊ የሆነ ንግድ ለመፍጠር እንደሚሰራ ንጉሱ አረጋግረጠዋል፡፡
ህዝባችን ኢከኖሚያችን በኮሮና ምክንያት አሁን እየተጎዳ ነው ያሉት ንጉሱ በአለም አቀፍ ትብብር ለመቋቋም የምንችለውን እየሰራን ነው ብለዋል ንጉስ ሳልማን፡፡
የቡድን20 አባል ሀገራት ስብሳባ ለመጀመሪያ ጊዜ በሳኡዲ አረቢያ ሰብሳቢነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡