ሲጓጓዝ የነበረው የሰብዓዊ እርዳታ ወደ መቀሌ እየገባ ነው-የዓለም የምግብ ፕሮግራም
የዓለም የምግብ ፕሮግራም በትግራይ 2.1 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል
የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ እሰካሁን ከ35 በላይ የድርጅቱ ሰራተኞች “መታፈናቸውን” መግለጹ የሚታወስ ገልጾ ነበር
ለሁለት ሳምንት ወደ ትግራይ ሲጓጓዝ የነበረ የሰብዓዊ እርዳታ ወደ መቀሌ እየገባ መሆኑን የዓለም ምግብ ድርጅት ገለጸ፡፡
“አሁን በትግራይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን 2.1 ሰዎች ለመድረስ 1ሺህ ሜትሪክ ቶን የህይወት አድን ምግብ ማዳረስ ያስፈልጋል”ም ብሏል የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትዊትር ገጹ ላይ ባሰፈረው መረጃ፡፡
የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሚያደርገው የእርዳታ ስርጭትን የቀጠለ ቢሆንም አሁንም ድረስ በመዳረሻዎች ችግሮች እየገጠሙኝ ነው ሲል ባለፈው ሳምንት መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡
በችግሮቹ ምክንያት የህይወት አድን አቅርቦቶች ስራው “ወደ ኋላ ቀርቷል” በማለት በትግራይ የዓለም ምግብ ፕሮግራም የአስቸኳይ ጊዜ አስተባባሪ ቶሚ ቶምፕሰን መናገራቸውንም እንዲሁ የሚታወስ ነው፡፡
በአሁኑ ሰአት በክልሉ የተወሰኑ ዞኖች “ውጊያው መቀጠሉን” እና ውጊያውን ተከትሎ ከ35 በላይ የድርጅቱ ሰራተኞች “መታፈናቸውን” አስተባባሪው በሳተላይት ስልክ ከመቀሌ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቦ ነበር፡፡
ግጭቱ በትግራይ ክልል ከተጀመረ ከ8 ወራት በኋላ የፌደራል መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም አውጆ የትግራይ ክልልን ለቆ መውጣቱ ይታወሳል፡፡ መንግስት ከትግራይ ክልል የወጣው ለትግራይ ቀውስ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት መሆኑን በወቅቱ ገልፆ ነበር፡፡
መንግስት ሰራዊቱን ከመቀሌ ማስወጣቱን ካስታወቁ በኋላ የህወሓት ኃይሎች መቀሌንና ሌሎች የክልሉን አካባቢዎች ተቆጣጥረዋል፡፡ መንግስት በትግራይ እርዳታ ለማድረግ ለሚፈልጉ አካላት እርዳታውን እንዲያደርሱ እንደሚያመቻችም ማስታወቁ ይታወሳል፡፡