በ’ምርጫ 2013’ ዙሪያ ያሉት ዋናዋና እውነታዎች የሚከተሉት ናቸው
ኢትዮጵያ 6ኛውን ሀገርአቀፍ ምርጫ በመጭው ሰኞ ታካሂዳላች፡፡ ምርጫ 2013ን የተመለከቱ እውነታዎችን የሚከተሉት ናቸው፡-
-በኢትዮጵያ ህገመንግስት መሰረት ምርጫ በየ5 አመቱ የሚካሄድ ሲሆን 6ኛ ምርጫ በኮሮና ወረርሽ ምክንያት በአንድ አመት መራዘሙ ታወሳል፡፡
-49 የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫው ለመወዳደር ከቦርዱ ፍቃድ አግኝቷል
-ፍቃድ ካገኙት መካከል 47ቱ የምርጫ ምልክት ወስደው የምርጫ ክርክር ሲያካሂዱ ቆይተዋል
-ገዥው ፓርቲ ብልጽግና 2799 እጩ በማቅረብ በእጩ ብዛት ቀዳሚ ሆኗል
-ምርጫው በ673 የምርጫ ክልሎች ይካሄዳል
-በጸጥታ ችግርና ከፖለቲካ ፓርቲዎች በቀረበ ቅሬታ ምክንያት በ27 የምርጫ ክልሎች ምርጫ አይካሄድም
-በ27ቱ የምርጫ ክልሎች፣ በሶማሌ እና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ (ለሕዝበ ውሳኔ) ጳጉሜ 1 ድምጽ ይሰጣል
-ፓርቲዎች ያቀረቡት እጩዎች ብዛት 9327
-ፓርቲዎች በምርጫው 1976 ሴት እጩዎችን አስመዝግበዋል
-በመርጫው 95 የአካል ጉዳተኞች በእጩነት ቀርበዋል
-ምርጫው በሁለት ዙር ሰኔ 14ና ጳጉሜ 1 ቀን ይካሄዳል
-በትግራይ በግጭቱ ምክንያት አጠቃላይ ምርጫው በትግራይ አይካሄድም
-ትግራይ ክልል ምርጫ ባለመካሄዱ ምክንያት በ38 የፓርላማ ወንበሮች ክፍት ይሆናል
- ሰኔ 14 በሶማሌ ክልል ምርጫው አይካሄድም
-ምርጫውን 45ሺ ታዛቢዎች ይታዘቡታል
- ምርጫ ቦርድ ከመንግስት ያገኘውን ከ98 ሚሊዮን በላይ ብር ለፓርቲዎች አከፋፍሏል
-በዘንድሮው አጠቃላይ ምርጫ 37.4 ሚሊዮን መራጭች ተመዝግበዋል
-የምርጫ ውጤት በየምርጫ ጣቢያው በማግስቱ ለህዝብ ይፋ ይሆናል
-የምርጫው አጠቃላይ ጊዜያዊ ውጤት ምርጫው ከተደረገ በኋላ በ10 ቀናት ውስጥ ይፋ ይሆናል
በምርጫ 2013፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች 547 መቀመጫዎች ባሉት የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት (ፓርላማ) መቀመጫ ለማግኘት ይወዳደራሉ፡፡