ምርጫ ቦርድ የአጠቃላይ የምርጫ ጊዜያዊ ውጤት በ10 ቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ ይሆናል ብሏል
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በሰጠው መግለጫ ምርጫ 2013 ለመታዘብ 45ሺ ታዛቢዊች ፍቃድ መውሰቸውን አስታውቋል፡፡ የቦርዱ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ሶሊያና ሽመልስ ምርጫውን ለመታዘብ ባጅ ከወሰዱት መካከል 167 የሲቨል ማኅበር ተቋማት መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ምርጫው በ372 የምርጫ ክልሎች ይካሄዳል ብለዋል ሶሊያና፡፡የደቡብ ምዕራብ ህዝበ ውሳኔን በተመለከተ እስካሁን ከዞኖቹ ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ የተወሰነ አዲስ ውሳኔ አለመኖሩን ሶልያና ሽመልስ ተናግረዋል፡፡
ሶሊያና ቦርዱ የቀረበውን ቅሬታ እየመረመረ መሆኑንና አዲስ ውሳኔ የሚኖር ከሆና በቀጣይ ያሳውቃል ብለዋል፡፡
ሶሊያና ሽመልስ በምርጫው በ27 የምርጫ ክልሎች መራጮች ድምጽ እንደማይሰጡ ገልጸዋል፡፡
በሶማሊ ክልል በሁሉም ምርጫ ክልሎች፣ በአማራ ኤፌሶን፣ አንኮበር ማጀቴ እንዲሁም በአርማጭሆ፣ በቤኒሻንጉል ደግሞ መተከል እና ከማሺ ሰኔ 14 መራጮች ድምፅ የማይሰጡባቸው የምርጫ ክልሎች መሆናቸውንም ነው የምርጫ ቦርድ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች አማካሪ ሶልያና ሽመልስ የተናጋሩት፡፡
ከመራጮች ምዝገባ እና ከጸጥታ ችግር እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ ጋር በተያያዘ ድምፅ የማይሰጥባቸው የምርቻ ክልልሎች እንደሚኖሩ ቦርዱ ቀደም ሲል ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡
የምርጫ ውጤትን በተመለከተ ምርጫው በተካሄደ በማግስቱ የምርጫው ውጤት በየምርጫ ጣቢያው ለህዝብ ይፋ ይሆናል ያሉት ሶልያና ሽመልስ፤አጠቃላይ የምርጫ ጊዜያዊ ውጤት ደግሞ ምርጫ ቦርድ በ10 ቀናት ውስጥ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል ብለዋል፡፡