ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰንን “አለሁልህ” ያለችው የቱርክ ገጠራማ መንደር
የመንደሩ ነዋሪዎች “ልጃችን” ብለው ሚጠሩትን ቦሪስ ጆንሰንን በማንኛውም ሰዓት ተቀብለው ለማስተናገድ ዝግጁ ነን ብለዋል
“ካልፋት” የተባለችው የቱርክ መንደር የቦሪስ ጆንሰን ቅድመ አያቶች የትውልድ ቦታ ነች
የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ብቻቸውን በቀሩብት፤ ካቢኔያቸው እና የፓርቲያቸው መሪዎች እሳቸውን ለመተካት በሚሯሯጡበት ወቅት ቱርክ ውስጥ የምትገኝ አንድ ገጠራማ መንደር “አለሁለህ” ማለቷ ተሰምቷል።
የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቅድመ አያቶች የትውልድ ቦታ የሆነቸው በቱርክ ሻንኪሪ ግዛት ውስጥ የምትገኘው የካልፋ መንደር ነዋሪዎች ቦሪስ ጆንሰን በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ድጋፍ በመስጠት ከጎናቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
የመንደሩ ነዋሪዎች “እኛ ሁሌም ከቦሪስ ጆንሰን ጎን ነን ከሻክሪ” በሚል መሪ ቃል ስልጣናቸውን እንደሚለቁ ላስታወቁት ቦሪስ ጆንሰን ያላቸውን ድጋፍ እየገለጹ ነው።
የካፋት መንደር ነዋሪዎች፣ የመንደሩ ከንቲባና እና የካልፋት ፋውዴሽን መግለጫን ያነበበው ሲናን ክራካክ፤ ቦሪስ ጆንሰንን በማንኛውም መንግድ መደገፍን ይቀጥላል ብሏል።
ቦሪስ ጆንሰን በሁሉም ነገር እስከ መጨረሻው ትእግስተኛ መሆን እንዳለባቸው የመከሩት የመንደሩ ነዋሪዎች፤ “በማንኛውም ሰዓት ልጃችንን (ቦሪስ ጆንሰንን) ለማስተናገድ ዝግጁ ነን” ብለዋል።
በኦቶማን ኢምፓየር ወቅት የሀገር ውስጥ ሚኒስትር የነበሩት አሊ ከማል የልጅ ልጅ የሆኑት የቦሪስ ጆንሰን አያት ሰታንሊይ ጆንሰን በሻኪሪ ግዛት በምትገኘው ካልፋት መንደር ነው የተወለዱት።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን በአንድ ወቅት ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሴት አያታቸው በኦቶማን ቱርክ ወቅት በባርነት ተሸጠው ሄደው እንደነበረ ተናግረው ነበር።
ቁልፍ የስልጣን አጋሮቻቸውን ጭምር ያጡት፤ የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን አጣብቂኝ ውስጥ በመግባታቸው ባሳለፍነው ወር ስልጣናቸውን እንደሚለቁ መግለጻቸው ይታወሳል።
ቦሪስ ጆንሰን ስልጣን አንደሚለቁ ማሳወቃቸውን ተከትሎ በርካታ ዩክሬናውያው ዜግነት እንዲሰጣቸው እና የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ የድጋፍ ድምጽ በማሰባሰብ ላይ እንደሆኑም ይታወቃል።