ስልጣን እንደሚለቁ ያሳወቁት ቦሪስ ጆንሰን ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ዩክሬን ሊጓዙ ነው
ቦሪስ ጆንሰን ወደ ኪቭ የሚያቀኑት “ኃላፊነት ተሰምቷቸው ነው” ተብሏል
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ዩክሬን ካቀኑ ሶስተኛቸው ነው
የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ዩክሬን ሊጓዙ መሆኑን አስታወቀ።
ቦሪስ ጆንሰን በነበረባቸው ጫና ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ጫፍ ላይ መድረሳቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ለሶስተኛ ጊዜ ወደ ኪቭ ሊጓዙ መሆኑ ተረጋግጧል።
ቦሪስ ጆንሰን ወደ ኪቭ የሚያቀኑት ሀገራቸው ለዩክሬን ያልተቆጠበ ድጋፍ እንደምታደርግ ለማረጋገጥ እንደሆነ ተገልጿል።
ተሰናባቹ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ዩክሬን የሚያደርጉት ጉብኝት የመጨረሻቸው እንደሆነም ነው የተገለጸው። ቦሪስ ጀንሰን እስካሁን ሁለት ጊዜ ወደ ዩክሬን መጓጓቸው የሚታወስ ሲሆን በዚህ ድርጊታቸውም የሞስኮ ባለስልጣናት ክፉኛ ተቀይመዋቸዋል።
የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር ለዩክሬን በሚደረግ ድጋፍ ዙሪያ እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
አሁን ላይ ቦሪስ ጆንሰን ወደ ዩክሬን እንደሚሄዱ ማሳወቃቸው ኃላፊነት የሚሰማቸው ያደርጋቸዋል ሲል ዴይሊ ኤክስፕረስ ዘግቧል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ወደ ዩክሬን ለመጓዝ ያሰቡት ዝም ብለው ኃላፊነታቸውን መልቀቅ አላስችል ብሏቸውና ሃላፊነት ተሰምቷው እንደሆነም ነው የተገለጸው።
ተሰናባቹ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ጋር አርብ ዕለት በስልክ መነጋገራቸው ተሰምቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ጆንሰን ከአሁን ቀደም ፈጽመዋቸዋል ከተባሉ የዲሲፕሊን ግድፈቶች ጋር በተያያዘ ስልጣን እንዲለቁ ጫናዎች ሲደረጉባቸው ነበረ።