ከሀማስ ጥቃት በኋላ ወደ እስራኤል የሚያደርጉትን በረራ ያገዱት አየር መንገዶች የትኞቹ ናቸው?
በግጭቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ በረራዎች ተስተጓጉለዋል
ሀማስ ከእስራኤል ጋር ለመነጋገር ፍቃደኝነቱን ቢገልጽም ጋዛን ለመክበብ እየተንቀሳቀሰች ያለችው እስራኤል ማጥቃቷን ቀጥላለች
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ ከአራት ቀናት በፊት በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በርካታ አየር መንገዶች ወደ ቴል አቪቭ የሚያደርጉትን ጉዞ አግደዋል።
በግጭቱ ምክንያት በመቶዎች የሚቆጠሩ በረራዎች መስተጓጎላቸውን ሮይተርስ በግቧል።
በረራ ያገዱት አየር መንገዶች የሚከተሉት ናቸው፦
አፍሪካ
ሮያል ኤየር ማርኮ(ሞሮኮ)
አሜሪካ
ዴልታ ኤየርላይንስ(አሜሪካ)
አሜሪካን ኤየርላይንስ(አሜሪካ)
ኤየርካናዳ(ካናዳ)
እስያ
ሃይናን ኤየርላይንስ(ቻይና)
ካቲ ፖሲፊክ(ሆንግ ኮንግ-ቻይና)
ኮሪያን አየር (ደቡብ ኮሪያ)
አውሮፖ
ሉፍታንዛ (ጀርመን)
ርያንኤየር( አየርላንድ)
ብሪቴን ኢዚ ጄት(ብሪቴን)
ኤየር ፍራንስ(ፈረንሳይ)
ፊን ኤየር(ፊንላንድ)
ሀንጋሪያን ዊዝ ኤየር(ሀንጋሪ)
ቲኤፒ(ፖርዩጋል)
ኤየር ኢሮፖ(ስፔን)
ፒኦቲ(ፖላንድ)
መካከለኛው ምስራቅ
ኢትሃድ አየርመንገድ(አረብ ኢምሬትስ)
ገልፍ ኤየር (ባህሬን)
ሀማስ ከጋዛ ሮኬቶች በማስወንጨፍ እና በታጣቂዎቹ የእስራኤልን ድንበር በመጣስ ባደረሰው "ከባድ እና ያልተጠበቀ" ጥቃት ሳቢያ እስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ውስጥ ከገቡ ዛሬ አራተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል።
ይህ ጥቃት በ50 አመታት ውስጥ ሀማስ ከሰነዘራቸው ጥቃቶች ውስጥ እጅግ ከባዱ መሆኑ ተገልጿል።
የሀማስን ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በሀማስ መቀመጫ በሆነችው ጋዛ ላይ ከባድ የአየር ጥቃት እያደረሰች ነው፤ጋዛን በመክበብ ጥቃት አድራሾችንም ለመግደል ወስናለች።
እስራኤል ጋዛን ለመክበብ በምታደርገው ጥረት በደቡባዊ እስራኤል ከፍተኛ ጦር አሰማርታለች።
እስካሁን በጦርነቱ በእስራኤል 900 ሰዎች የሞቱ ሲሆን በጋዛ በኩል ደግሞ 700 ሰዎች ተገድለዋል።
አሜሪካን ጨምሮ በርካታ ምዕራባውያን ሀገራት ሀማስን በማውገዝ እስራኤልን እንደሚደግፉ ባወጧቸው መግለጫዎች ገልጸዋል።
ሩሲያ እና የአረብ ሀገራት በአንጻሩ ማንንም ሳያወግዙ ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።
ሀማስ ከእስራኤል ጋር ለመነጋገር ፍቃደኝነቱን ቢገልጽም ጋዛን ለመክበብ እየተንቀሳቀሰች ያለችው እስራኤል ማጥቃቷን ቀጥላለች።