“አይረን ዶም” እስራኤልን እየታደገ ያለው ዘመናዊ መሳሪያ ምንድን ነው?
ሃማስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል የተኮሰ ሲሆን አብዛኛው በአይረን ዶም አየር ላይ ወድመዋል
እስራኤልን ከጥፋት የሚታደገው አይረን ዶም የአየር መከላከያ ስርዓት እንዴት ይሰራል?
ካሳለፍነው ቅዳሜ ጀምሮ ከ3 ሺህ 500 በላይ ሮኬቶች ከጋዛ ወደ እስራኤል መተኮሳቸውን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል
እስራኤላውያን ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል በየምሽጉ ሲሸሹ፤ የእስራኤል የአየር መከላከያ ስርዓት “አይረን ዶም” የአጭር ርቀት ሮኬቶችን እና የሞርታር ተኩሶችን በመከላከል ረገድ ትልቁን ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
አይረን ዶም ራፋኤል አድቫን ሲስተም በተባለ ኩባንያ እና በእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪዎ በጋራ የተሰራ የአየር መከላከያ መሳርያ ነው።
አይረን ዶም ወደ ወደ አገለግሎት ከገባ ከፈረንጆቹ 2011 ወዲሀ ለሀገሪቱ የጀርባ አጥንት እና ወሳኝ ጦር መሳሪያ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል።
አይሮን ዶም ከ 4 ኪሎ ሜትር እስከ 70 ኪሎ ሜትር ርቀቶችን የሚወነጨፉ የአጭር ርቀት ሮኬቶችን እና የመድፎችን ለማምከን እና ለማጥፋት የተሰራ መሳርያ ነው።።
የእስራኤል ጦር እንደገለጸው አይረን ዶም በአሁኑ ጊዜ ካለፉት ዙሮች ጋር ተመሳሳይ በሆነ አቅም እየሰራ ሲሆን ስኬታማነቱም እስከ 90 በመቶ ድረስ መሆኑን አስታውቋል።
አይረን ዶም የመከላከያ ስርዓት እንዴት ነው የሚሰራው?
አይረን ዶም የመከላከያ ስርዓት በሚሳይል መከላከያ ባትሪዎች የሚሰራ ሲሆን እያንዳንዳቸው ሶስት ዋና ዋና ክፍሎችን ያቀፉ ናቸው። እነዚህ ባትሪዎች ከባትሪው በ72 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የአጭር ርቀት ሮኬት እና የሞርታር ጥቃቶችን መከላከል ይችላሉ።
አይረን ዶም የመከላከያ ስርዓት ተንቀሳቃሽ በመሆናቸው ከመጠቀም በፊት መጀመሪያ ወደሚፈልጉበት ቦታ ይንቀሳቀሳሉ።
የመከላከያ ስርአቱ ስራ የሚጀምረው በራዳር ዩኒት የሚመጣውን ሚሳኤል ፍጥነት እና መንገዱን ወደ ባትሪ መቆጣጠሪያ ማዕከል ለማስተላለፍ ነው።
በመቆጣጠሪያ ማዕከሉ ውስጥ ያሉ ኮምፒተሮች ሚሳኤሉ በምን ፍጥነት እንደሚጓዝ እና የት እንደሚያርፍ የሚያሰሉ ሲሆን፤ ህዝብ በሚበዛባቸው አካባቢዎች እንደሚመታ ከተረጋገጠ መከላከያ ሮኬት ከማስጀመሪያው ላይ ይነሳል።
አይረን ዶም የሚያስወነጭፈው የመከላከያ ሚሳዔል ወደ እስራዔል የተተኮሰውን ሚሳዔል አየር ላይ የሚያመክነው አጠገቡ በመፈንዳት እና ንጹሃን ዜጎች ላይ የሚያደርሰውን አደጋ በመቀነስ ነው።
አይረን ዶም የመከላከያ ስርዓት ከፈረንጆቹ 2021 ወዲህ ብቻ ህዝብ ላይ ጉዳት ሚያደርሱ የሚችሉ ከ2 ሺህ 400 በላይ ሚሳዔሎችን አምክኗል።