የእስራኤል እና የፍልስጤም ሃማስ ጦርነት፤ ምን አዳዲስ ክስተቶች አሉ?
እስራኤል በትናንትናው እለት ብቻ በ1 ሺህ የጋዛ ኢላማዎች ላይ የአየር ድብደባ ፈጽማለች
በእስራኤል 900 ሰዎቸ በጋዛ ደግሞ 700 ፍልስጤማውያን እስካሁን በጦርነቱ ሞተዋል
ሃማስ ባሳለፍነው ቅዳሜ በእስራኤል ላይ ያለተጠበቀ እና ድንገተኛ ጥቃት መሰንዘረሩን ተከትሎ በእስራኤልና በፍልስጤም መካከል የተጀመረው ጦርነት ዛሬ አራተኛ ቀኑን ይዟል።
በሃማስ ጥቃት እና በእስራኤል የአየር ድብደባ ከሁለቱም ወገኖች የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ1 ሺህ 600 ማለፉ ተነግሯል።
የእስራኤል መከላከከያ ኃይል ባወጣው መረጃ መሰረት በሃማስ ጥቃት የሞቱ እስራኤላውኝ ቁጥር 900 የደረሰ ሲሆን፤ ከ2 ሸህ በላይ ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
በእስራዔል ከተገደሉ ሰዎች መካከል የአርጀንቲና፣ የካምቦዲያ፣ እና የአሜሪካን ጨምሮ የሌሎች ሀገራት ዜጎችም እንደሚገኙበት ተገልጿል።
አሜሪካ በሃማስ ጥቃት 11 ዜጎቿ እንደተገደሉባት ትናንት አስታውቃለች።
የፍልስጤም ባለስልጣናት በሰጡት መረጃ ደግሞ በእስራኤል የአየር ድብደባ የሞቱ ፍልስጤማውያን ቁጥር 700 መድረሱን የገለጹ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ 143 ህጻት እና 105 ሴቶች ይገኙበታል።
የተመድ የስደቶች ኤጀንሲ እንዳስታወቀው በእስራኤል የአየር ድብደባ 187 ሺህ ሰዎች ከጋዛ መፈናቀላቸውን እና ከእነዚህም 137 ሺህ ሰዎች በ84 ትምህርት ቤቶች ውስጥ መጠለላቸውን አስታውቋል።
እስራኤል በጋዛ የምታካሂደውን የአየር ድብደባ የቀጠለች ሲሆን፤ አዳሩን በካሄደችው የአየር ድብደባ ሁለት የፍልስጤም ጋዜጠኞች ተገድለዋል።
እስራኤል በተትናትናው እለት ብቻ በጋዛ ውስጥ በሚገኝ 1 ሺህ የሃማስ ኢላማዎች ላይ የአየር ድብደባ መፈጸሟ ተነግሯል።
የእስራዔል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ትናት ምሽት በሰጡት መግለጫ፤ በጋዛ እየተካሄደ ያለው የአየር ድብደባ ገና ጅማሮ ነው ብለዋል።
በጋዛ የምታዩት ውድመት ገና የመጀመሪያው ነው ያት ኔታንያ፤ የአየር ድብደባው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል።
የአሜሪካ የጋራ ግብረ ኃይል ዋና አዛዥ ጄንራል ቻርልስ በሮወን፤ ኢራን በጦርነቱ ውስጥ ከመሳተፍ እንድትቆጠብ አሳስበዋል።
ኢንዶኔዤያ ዜጎቿ በአስቸኳይ እስራዔልን ለቀው እንዲወጡ ማሳሰቢያ ሰጥታለች።