አሜሪካ ፕረዝዳንታዊ ምርጫ ከማክሰኞ ዕለት ውጪ እንዳይካሄድ የሚከለክል ህግ አላት
የዓለማችን ልዕለ ሀያል ሀገር አሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርቶታል።
በሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ እና ዲሞክራቷ ካማላ ሀሪስ መካከል የሚካሄደው ይህ ምርጫ የፊታችን ማክሰኞ ይካሄዳል።
አሜሪካ በየ አራት ዓመቱ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት፣ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ህግ አውጪ ምክር ቤት አባላት ምርጫን አንዴ ታካሂዳለች።
ይህ ምርጫ ከፈረንጆቹ 1845 ጀምሮ በመካሄድ ላይ ሲሆን ምርጫው ሁልጊዜ ማክሰኞ ዕለት ብቻ ይካሄዳል።
በሀገሪቱ ምርጫ ህግ መሰረት ምርጫው በየ አራት ዓመቱ ህዳር ወር ላይ በመጀመሪያው ሳምንት ማክሰኞ ዕለት ብቻ እንዲካሄድ የሚያስገድድ ህግ አላት።