በሊባኖስ ከፈነዳው የኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ጀርባ ያለችው ክሪስቲያና አርሲዲኮኖ ማን ናት?
በሊባኖስ ከሰሞኑ በኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ፍንዳታ 37 ሰዎች ሲሞቱ ከ2 ሺህ በላይ ደግሞ ቆስለዋል
መሳሪያዎቹን ዲዛይን በማድረግ ተሳትፋለች የተባለችው ክርስቲያና ሰባት ቋንቋዎችን ከመናገሯ ባለፈ በፊዚክስ የዶክትሬት ድግሪ ባለቤት ናት
በሊባኖስ ከፈነዳው የኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ጀርባ ያለችው ክሪስቲያና አርሲዲኮኖ ማን ናት?
በያዝነው ሳምንት መጀመሪያ ቀናት ላይ በሊባኖስ በርካታ ቦታዎች ላይ የኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ፈንድተው በዜጎች ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል፡፡
ፍንዳተዎቹ የተከሰተባቸው የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ከታይዋን በተለይም ጎልድ አፖሎ ከተሰኘው ኩባንያ የተገዙት ሲሆን በፍንዳታው ምክንያት 37 ሰዎች ሲገደሉ ከ2 ሺህ በላይ ያል ደግሞ ቆስለዋል፡፡
በርካታ ሀገራት ይህ ፍንዳታ በሴራ የተደረገ እና ለየት ያለ ክስተት መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ጉዳዩ ብዙዎችን ትኩረት ስቧል፡፡
በተለይም ፍንዳታዎቹ አገልግሎት እየሰጡ ከነበሩበት ቦ ይከሰቱ እንጂ በሌላ ሀገር ሆነው መሳሪያዎቹን የሚቆጣጠሩ እና እንዲፈነዱ የሚያደርግ ዲዛይን እንደተሰራላቸውም ተገልጿል፡፡
በሊባኖስ የፈነዱት እነዚህ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በታይዋን ቢሰሩም ምርቶቹን ግን ዳግም ዲዛይን ያደረገ አንድ ተቋም እንዳለ ተገልጿል፡፡
የጣልያን እና የሀንጋሪ ዜግነት ያላት ክርሲቲያናባርሶኒ አርሲዲያኮኖ የተመሰረተ ቢኤሲ የተሰኘ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መስራች እና ባለቤት ናት፡፡
የ49 ዓመት እድሜ ያለት ይህች ሴት ሰባት ቋንቋዎችን አቀላጥፋ የምትናገር ሲሆን ኩባንያዋ በሊባኖስ ከሰሞኑ የፈነዱትን የኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ዲዛይን አድርጓል ተብሏል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ በጣልያኗ ሲሲሊ ተወልዳ የደገችው ይህች ሴት በፊዚክስ ሙያ የዶክትሬት ድግሪዋን ከለንደን ዩንቨርሲቲ ያገኘች ሲሆን በሙያዋ ብዙም ሳትገፋበት ቆይታለች፡፡
የተመድ አቶሚክ ድርጅትን ጨምሮ በበርካታ የዓለማችን ተቋማት እንደሰራች ብትናገርም ተቋማቱ ሰራተኛቸው እንዳልሆነች ለሮይተርስ ተናግረዋል፡፡
በሀንጋሪ መዲና ቡዳፔስት ከተማ ትኖራለች የተባለችው ይህች ሴት በሊባኖስ የፈነዱት የኮሙንኬሽን መሳሪያዎችን ኩባንያዋ እንዳልሰራቸው እና የእሷ ስራ ምርቶቹን የማስተላለፍ ስራ ብቻ እንደነበርም ተናግራለች፡፡
እንስቷ ይህን ከተናገረች በኋላ ደብዛዋን ያጠፋች ሲሆን በመኖሪያ ቤቷ እየኖረች እንዳልሆነ እና የሀንጋሪ የደህንነት አካላት እየተከታተሏት ነውም ተብሏል፡፡
በሊባኖስ በኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ስለተፈጸመው ጥቃት እስካሁን የምናውቀው
የኩባንያው ዌብሳይት ከኢንተርኔት ለይ የወረደ ሲሆን ከዚህ በፊት ስለ እሷ የተናገረቻቸው ነገሮች ሁሉ ሀሰተኛ መሆናቸውን በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡
በቡዳፔስት ለሁለት ዓመት የሚቆይ የስነ ስዕል ሙያ ትምህርት ለመማር የተመዘገበች ቢሆንም ትምህርቱን እንዳቋረጠች፣ በሊቢያ ለማማከር ስራ ቀጥሯት የነበረው ኩባንያም ውሉን ወዲያው እንዳቋረጠ እንዲሁም እሷን የሚውቋት ሰዎች ሁሉ ስለ እሷ ደፍረው ሊናገሩት የማይችሉት ነገር አንደሌላቸውም ለዚሁ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ ሚዲያዎችን ጨምሮ በበርካቶች እየተፈለገች የሆነችው ይህች ሴት የት እንዳለች አይታወቅም፡፡
ሂዝቦላህ ከሰሞኑ ስለደረሰው የኮሙንኬሽን መሳሪያዎች ፍንዳታ በሰጠው መግለጫ ፍንዳታው የእስራኤል ደህንነት ከምርቶቹ አምራች ኩባንያ ጋር በመመሳጠር እንደፈጸመችው መናገሩ አይዘነጋም፡፡