በ4 ቢሊዮን ዶላር ምዝበራ በአሜሪካ የምትፈለገው ኢግናቶቫ ማን ነች?
በኤፍቢአይ ንግስቷ የሚል ቅጽል ስም የተሰጣት ይህችን ሴት ለጠቆመ 5 ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ አዘጋጅቷል
የዘር ሀረጓ ከቡልጋሪያ የሚመዘዘው ይህች ሴት ደብዛዋ ከጠፋ ዓመታት ቢቆጠርም ራሷን ሳትቀይር እንዳልቀረች ይጠረጠራል
በ4 ቢሊዮን ዶላር ምዝበራ በአሜሪካ የምትፈለገው ኢግናቶቫ ማን ነች?
ሩጃ ኢግናቶቫ የዘር ሀረጓ ከምስራቅ አውሮፓዊቷ ቡልጋሪያ የሚመዘዝ ሲሆን በዜግነት ጀርመናዊ ናት፡፡
ዋን ኮይን በሚል ስም የምናባዊ ገንዘብ ድርጅት አቋቂሜያለሁ በሚል በአጭር ጊዜ ውስጥ 4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ገንዘብ መዝብራለች ተብሏል፡፡
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ይህች ሴት የ44 ዓመት እድሜ ያላት ሲሆን ከፈረንጆቹ 2017 ጀምሮ በአካል አይተናታል የሚል ሰው አልተገኘም፡፡
ሴትዮዋ ደብዛዋ የጠፋው የአሜሪካው ፌደራል ወንጀል ምርመራ ቢሮ የእስር ማዘዣ ካወጣበት ዕለት ጀምሮ ሲሆን መጀመሪያ ላይ ኢግናቶቫን ለጠቆመ 100 ሺህ ዶላር ሽልማት ተዘጋጅቶላት ነበር፡፡
የሩሲያው ምናባዊ ገንዘብ ተቋም በኢትዮጵያ የዳታ ማዕከል ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ
ይሁንና ይህችን ሴት አየሁ የሚል መጥፋቱን ተከትሎ ለጠቋሚዎች የሚሰጠውን ገንዘብ ወደ 200 ሺህ ዶላር ከፍ ቢልም አሁንም ጠቋሚ አልተገኘም፡፡
ኤፍቢአይ አሁን ላይ ይህችን ከፍተኛ ገንዘብ የመዘበረች እንስት ለጠቆመኝ 5 ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ ለማለት ተገዷል፡፡
ሩጃ ኢግናቶቫ ገንዘቡን ከመዘበረች በኋላ በቀጥታ ወደ ቡልጋሪያ መዲና ሶፊያ እንደተጓዘች ፍንጮች እንደተገኙ ተገልጾ ነበር፡፡
ይሁንና ለዓመታ በተደረጉ ተከታታይ ምርመራ ኢግናቶቫን ያየ ሰው ያልተገኘ ሲሆን ባንድ በኩል በማፊያዎች ሳትገደል እንዳልቀረች ተጠርጥሯል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ ቢሊየነሯ ሩጃ ኢግናቶቫ ማንነቷን ቀይራ በቡልጋሪያ ቅንጡ ህይወቷን እየመራች እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ኤፍቢአይ የሩጃ ኢግናቶቫ ትክክለኛ ሁኔታ በቅርቡ እንደሚደርሰው በመተማመን አድራሻዋን ለጠቆመ 5 ሚሊዮን ዶላር ጉርሻ ማዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡