በአፍሪካ በዚህ አመት 30ሺ ገደማ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መጠርጠራቸውን ድርጅቱ አስታወቀ
የተመድ የጤና አካል የሆነው ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት እንደገለጸው ከ800 በላይ ሰዎች በተጠረጠረው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ህይወታቸውን አጥተዋል
ድርጅቱ በሽታው አለባቸው ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ አብዛኞቹ ዲሞክራሲያዊ የፐብሊክ ኮንጎ ውስጥ ናቸው ብሏል
በአፍሪካ በዚህ አመት 30ሺ ገደማ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ መጠርጠራቸውን ድርጅቱ አስታወቀ።
በአፍሪካ በዚህ አመት 30ሺ ገደማ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ተይዘዋል ተብለው ተጠርጥረው መመዝገባቸውን የአለም ጤና ድርጅት በትናንትናው እለት ገልጿል።
ድርጅቱ በሽታው አለባቸው ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ አብዛኞቹ ዲሞክራሲያዊ የፐብሊክ ኮንጎ(ዳአርሲ) ውስጥ ናቸው ብሏል። የተመድ የጤና አካል የሆነው ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት እንደገለጸው ከ800 በላይ ሰዎች በተጠረጠረው የዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ ህይወታቸውን አጥተዋል።
ድርጅቱ አክሎም የዲአርሲ ጎረቤት የሆነችው ቡሩንዲ በበሽታው በከፍተኛ ሁኔታ ተጠቅታለች ብሏል።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር በሚደረግ ንክኪ ይተላለፋል። በሽታው ብዙ ጊዜ የከፋ ጉዳት የማያስከትል ሲሆን አልፎ አልፎ ግን ገዳይ ነው። ጉንፋን አይነት ምልክት ያለው ይህ በሽታ በሰውነት ላይ በመግል የሞሉ እብጠቶችን ያስከትላል።
በድርጅቱ ሪፖርት መሰረት ከጥር እስከ መስከረም 15 ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ በመላው አፍሪካ 812 ሰዎች የሞቱ ሲሆን 29,342 ሰዎች ደግሞ በበሽታው ተጠርጥረዋል። በነሐሴ ወር ብቻ 2082 ሰዎች በሽታው የተገኘባቸው ሲሆን ይህ ቁጥር ከባለፈው ህዳር ወዲህ ከፍተኛ መሆኑን የአለም ጤና ድርጅት ገልጿል።
የአለም ባንክ ባለፈው ቅዳሜ እለት ወረርሽኙን ለመከላከል እንዲረዳቸው ለ10 የአፍሪካ ሀገራት 128 ሚሊዮን ዶላር እሰጣለሁ ብሏል።