የተለያየ አቋም የያዙት ሩሲያ እና አሜሪካ በጸጥታው ም/ቤት እንዴት ድምጸ ተአቅቦ አደረጉ?
ለአሜሪካ ተኩስ አቁም ማለት ሀማስ በድጋሚ ተደራጅቶ የጥቅምቱን አይነት ጥቃት እንዲፈጽም እድል መስጠት ነው
ሩሲያ በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ያቀረበችው ማሻሻያ ሀሳብ ባለመካተቱ ድምጸ ተአቅቦ አድርጋለች
በጋዛው የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ጉዳይ አሜሪካ እና ሩሲያ የተለያየ አቋም ያራምዳሉ።
አሜሪካ ጦርነቱን ቀስቅሷል ያለችው የፍልስጤሙን ታጣቂ ቡድን ሀማስ ለተፈጠረው ችግር ተጠያቂ ነው ትላለች። ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ ጋዛን እያስተዳዳረ ያለውን ሀማስን ከምድረ ገጹ ለማጥፋት በአየር እና በእግረኛ ጦር መጠነ ሰፊ ጦርነት የከፈተችውን እስራኤል በመደገፍ ላይ ነች።
ለአሜሪካ ተኩስ አቁም ማለት ሀማስ በድጋሚ ተደራጅቶ የጥቅምቱን አይነት ጥቃት እንዲፈጽም እድል መስጠት ነው።
በዚህ ምክንያት አሜሪካ የተኩስ አቁም ሀሳብን አትቀበልም።
ሩሲያ በአንጻሩ ግጭቱ የአሜሪካ የተሳሳተ የመካከለኛው ፖሊሲ ውጤት ነው ትላለች።
ሩሲያ በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ እና የሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ እንደምትፈልግ በተደጋጋሚ አሳስባለች።
በትናንተናው እለት በጋዛ የሰብአዊ እርዳታ እንዲገባ የሚያስችለው በተመድ የጸጥታው ምክርቤት በአረብ ኢምሬትስ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በ13 ድምጽ ድጋፍ ጸድቋል።
ሩሲያ እና አሜሪካ ግን ድምጽ ከመስጠት ታቅበዋል።
ሩሲያ በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ያቀረበችው ማሻሻያ ሀሳብ ባለመካተቱ ድምጸ ተአቅቦ አድርጋለች።
ሩሲያ እርዳታው በተገቢ ሁኔታ እንዲደርስ የውሳኔ ሀሳቡ ግጭት እንዲቆም የሚያደርግ አንቀጽ ማካተት አለበት የሚል ማሻሻያ ሀሳብ ነበር ያቀረበችው።
ነገርግን ይህ የውሳኔ ሀሳብ አሜሪካ በጥቅሉ የውሳኔ ሀሳቡን ውድቅ እንዳታደርገው ታስቦ ሳይካተት ቀርቷል።
የጸጥታው ምክርቤት በውሳኔ ሀሳቡ ላይ የሚደረገው ድምጽ የመስጠት ሂደት ባለፈው ሳምንት ለበርካታ ቀናት አራዝሞት ነበር።
ጽምጽ ከተሰጠ በኋላ የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ የውሳኔ ሀሳብ ያቀረበችውን የአረብ ኢምሬትስን ጥረት አድንቀዋል።
ወደ ጋዛ እርዳታ የሚገባው እርዳታ እንዲጨምር አሜሪካ ትሰራለች ያሉት አምባሳደሯ፣ ሀማስ ለሰላም አይጨነቅም፣ በጥቀምት ወር የፈጸመውን ጥቃት ድጋሚ መድገም ይፈልጋል የሚል ክስ አሰምተዋል።
የተመድ ዋና ጸኃፋ ማሳሳቢያን ተከትሎ የጸጥታው ምክርቤት በዚህ ወር መጀመሪያ አቅርቦት የጋዛ ተኩስ አቀም የውሳኔ ሀሳብ አሜሪካ በመቃወሟ አለመጽደቁ ይታወሳል።
እስራኤል በጋዛ እያደረገች ያለውን ጥቃት አጠናክራ ቀጥላለች።