ሚስቱን ሆን ብሎ ሌሎች ሰዎች እንዲደፍሯት ሲያመቻች የነበረው ሰው ታሰረ
ባልየው የማያውቃቸውን ሰዎች በበይነ መረብ አማካኝነት እየመለመለ ሚስቱን ሲያስደፍር ነበር ተብሏል
ባልየው ድርጊቱን ሲፈጽም የነበረው ሚስቱ ራሷን እንዳታውቅ የሚያደርግ መድሀኒት ያለ ፈቃዷ በመስጠት እንደሆነ ፖሊስ አስታውቋል
ሚስቱን ሆን ብሎ በሌሎች ሰዎች ሲያስደፍር የነበረው ሰው ታሰረ
ዶምኒክ ፒ በሚል ስያሜ የሚጠራው ሰው ፈረንሳዊ ሲሆን በፓሪስ ከሚስቱ እና ሶስት ልጆቹ ጋር ይኖራል።
በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለው ይህ ሰው ለዓመታት በሚስቱ ላይ የፈጸመው ድርጊት የዜና ሽፋን ማግኘቱን ተከትሎ በመላው ፈረንሳይ ቁጣ አገርሽቷል።
እንደ ፍራንስ 24 ዘገባ ከሆነ ይህ ሰው ለዓመታት እንግዳ ሰዎችን ወደ መኖሪያ ቤቱ በማምጣት ሚስቱን እንዲደፍሩ አድርጓል።
ግለሰቡ ድርጊቱን የሚፈጽመው ሚስቱ ራሷን እንድትስት እና ህመሞችን እንድትቋቋም የሚያደርግ ማደንዘዣ መድሀኒት ያለ ፍቃዷ እንድትወስድ በማድረግ ነውም ተብሏል።
ከ2011 ጀምሮ በተለያዩ ሰዎች ስትደፈር የነበረችው ሚስቱ በመጨረሻም ፖሊስ ግለሰቡን በሌላ ወንጀል ጠርጥሮት በቁጥጥር ስር ካዋለው በኋላ በስልኩ ላይ ባደረገው ምርመራ አማካኝነት ነበር ነጻ የወጣችው።
እንደ ፖሊስ ምርመራ ከሆነ የ72 ዓመት እድሜ ያላት ይህች ሴት በባሏ አመቻቺነት ባለፉት 10 ዓመታት ውስጥ 92 ጊዜ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ተፈጽሞባታል።
ወንጀሉን ከፈጸሙት 72 ሰዎች ውስጥም 51ዱ እንደተለዩ ፖሊስ አስታውቋል ተብሏል።
ባልየው ሚስቱን የሚደፍሩ ወንዶችን ለማግኘት ኢንተርኔትን ጭምር ይጠቀም እንደነበር ለፖሊስ የተናገረ ሲሆን ወንዶቹ ሚስቱን ሲደፍሩ የሚያሳዩ ምስሎችን እንደሚቀርጽም ተናግሯል።
ከደፋሪዎቹ ውስጥም ስድስቱ ሰዎች ደጋግመው በመምጣት የአስገድዶ መድፈር ወንጀሉን ፈጽመዋል የተባለ ሲሆን ሶስቱ ግን ወንጀሉን አንፈጽምም ብለው ተመልሰዋል ተብሏል።
በአዛውቷ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀሉን ፈጽመውታል ተብለው ከተጠረጠሩት ውስጥ የኩባንያ ስራ አስኪያጆች፣ ባለ ትዳሮች፣ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች፣ የከባድ ተሽከርካሪ ሾፌሮች እና ጋዜጠኞችም እንደሚገኙበት ተገልጿል።
ጉዳዩ በመላው ፈረንሳይ መነጋገሪያ የሆነ ሲሆን በአጥፊዎች ላይ ተገቢው ቅጣት እንዲጣል እየጠየቁ ይገኛሉ።
የጉዳቱ ሰላባ የሆነችው ሴትም ከሶስት ልጆቿ ጋር ፍርድ ቤት ዩተገኘች ሲሆን ችሎቱ በዝግ እንዲሆን ትፈልጊያለሽ ተብላ በዳኞች ስትጠየቅ " ችሎቱ በሚስጢር እንዲካሄድ የሚፈልጉት ወንጀለኞቹ እንጂ እኔ ሁሉም ነገር በግልጽ እንዲደረግ ነው የምፈልገው" ብላለች።