የኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ውጤት ዛሬ ይፋ ሆኗል
የኬንያ ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ዊያልየም ሩቶ በኬንያ የተካሄደውን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ አሸነፉ።
ዊሊያም ሩቶ ተቀናቃኛቸውን ራይላ ኦዲንጋን በ50.49 በመቶ በሆነ ድምስ ማሸነፉቸውን የምርጫ ኮሚሽኑ ይፋ አድርጓል።
ዊሊያም ሩቶ የኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢን በምርጫ ቀደም ብለው ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል።
ዊሊያም ሩቶ ተቀናቀኛቸውን ራይላ ኦዲንጋን በጠባብ ውጤት ሲመሩ ቆይተዋል። በምርጫው 22 ሚሊዮን ኬንያውያን ተመዝግበው ነበር።
በኬንያ እየተካሄደ ያለው ምርጫ በአብዛኛው ጥሩ የሚባል መሆኑን የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞ ኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
የኢጋድ በተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ በመላክ ምርጫውን እየታዘበ ይገኛል፡፡
በኬንያ በተለይም በፈረንጆቹ 2007 የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ በሀገሪቱ አመጽና እና ተቃውሞ ተነስቶ ነበር፡፡ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ኬንያ ፖሊስ የምርጫውን ውጤት ባለመቀበል በአደባባይ በወጡት ላይ የኃል ርምጃ ውስዳል፤ ሰዎችን ገድሏል፤ ቤት ለቤት በመዞር ፍተሻ በማድረግ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል ሲልም ሪፖርት አቅርቦ ነበር፡፡