ዊሊያም ሩቶ የኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ አስተዳደርን በምርጫ አሸነፉ
በዊሊያም ሩቶ እና ራይላ ኦዲንጋ መካከል ያለው የድምጽ ልዩነት በጣም ጠባብ የሚባል ነው
የኬንያን ምርጫ በጠባብ ልዩነት እየመሩ ያሉት ዊሊያም ሩቶ በናይሮቢያ በተካደው ምርጫ ተቀናቃኛቸውን አሸንፈዋል
የኬንያን ምርጫ በጠባብ ልዩነት እየመሩ ያሉት ምክትል ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ በናይሮቢ በተካደው ምርጫ ተቀናቃኛቸውን ራይላ ኦዲንጋን አሸንፈዋል፡፡
በኬንያ እየተካሄደ ባለው ምርጫ ተቀናቃኝ የሆኑት ምክትል ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ የኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ አስተዳደርን ማሸነፋቸውን የኬንያ የምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
የቀድሞ የናይሮቢ ህግ አውጭ የነበሩት ጆንሰን ሳካጃ ማክሰኞ እለት የተካሄደውን ምርጫ መሸነፋቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
በኬንያን ምርጫ ምክትል ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ከገዥው ፓርቲ እና ራይላ ኦዲንጋ ከተቃዋሚ ፓርቲ በምርጫው ከፍተኛ ፉክክር እያደረጉ ናቸው፡፡
በኬንያ እየተካሄደ ያለው ምርጫ በአብዛኛው ጥሩ የሚባል መሆኑን የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞ ኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
የኢጋድ በተጨማሪ የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ በመላክ ምርጫውን እየታዘበ ይገኛል፡፡
በኬንያ በተለይም በፈረንጆቹ 2007 የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ተከትሎ በሀገሪቱ አመጽና እና ተቃውሞ ተነስቶ ነበር፡፡ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ኬንያ ፖሊስ የምርጫውን ውጤት ባለመቀበል በአደባባይ በወጡት ላይ የኃል ርምጃ ውስዳል፤ ሰዎችን ገድሏል፤ ቤት ለቤት በመዞር ፍተሻ በማድረግ የሰብአዊ መብት ጥሰት ፈጽሟል ሲልም ሪፖርት አቅርቦ ነበር፡፡