የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ፈጣን ምላሸ እንዲሰጠው የወላይታ ወጣቶች ጠየቁ
የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ እሰከ ታህሳስ 10/2012 ዓ.ም. ምላሽ ካላገኘ፣ ከዚያ በኋላ በአከባቢው ለሚፈጠረው ችግር የደቡብ ክልል እናየፌደራል መንግሰት ሀላፊነት ይወስዳሉ ሲል ‘የላጋ’ ተብሎ የሚጠራው የወላይታ ወጣቶች ቡድን አስታውቋል፡፡
እራሱን የወላይታ ህዝብ የነፃነት ተጋይ አድርጎ የሚጠራው ‘የላጋ’ በመባል የሚታወቅ የወጣቶች ሰብሰብ የወላይታ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ያለበትን ደረጃ በተመለከተ ውይይት አካሂዷል፡፡
ከቀናት በፊት የወላይታ ዞን ምክር ቤት ባካሄደው አሰቸኳይ ጉባኤ የክልሉ ምክር ቤት በአጭር ጊዜ ውሰጥ ምላሸ ካልሰጠው ጉዳዩን ወደ ፌደሬሸን ምክር ቤት በአቤቱታነት እወሰደዋለሁ ማለቱ የሚታወስ ነው፡፡
በወጣቶቹ ዉይይትም ከጥያቄው መዘግየት ጋር የተያያዙ ሀሳቦች በስፋት ተነሰተዋል::
ለህዝቡ ጥያቄ አሰራርን በተከተለ መንገድ የደቡብ ክልል ምክር ቤት ምላሸ በመስጠት በ2012 ከሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ቀድሞ ህዝበ ውሳኔ እንዲያደራጅም ጠይቀዋል
መንግሰት ህግን አክብሮ ምላሸ ሊሰጥ ይገባል ያሉት ወጣቶቹ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በአከባቢው ሊፈጠር ለሚችለው ውጥረት የክልሉ እና የፌደራል መንግሰትን ተጠያቂ እንደሚያደርጉም ገልፅዋል፡፡
በውይይቱ ላይ አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረሰ አመራሮች የተገኙ ሲሆን በኦሮሞ ህዝብ የትግል ተሞክሮ እና በፌደራሊዝም ፅንሰ ሀሳብ ላይ ያተኮሩ ሀሳቦችን አቅርበዋል::
የኦሮሞ ፌደራሊሰት ኮንግረሰ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ በቀለ ገርባ የወላይታ ህዝብ ጥያቄ ረጅም አመትን ያሰቆጠረ በመሆኑ ይህን ሀሳብ ለመደገፍ በማሰብ እንደተገኙ ተናግረዋል።
ነገ ለሁላችንም የምትሆን በእኩልነት የምንኖርባትን ደሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ለመገንባት በቁርጠኝነት መንቀሳቀሰ እንደሚያሰፈልግም ተናግረዋል::
ወጣቶቹም በስተመጨረሻ ባለ 8 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት ውይይተቸውን የቋጬ ሲሆን፣ ሂደቱ ሰላማዊ መንገድን በተከተለ አካሄድ እንዲፈፀም ጥረታቸውን አጠናክረው አንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል፡፡
አል-ዐይን ሀዋሳ