ቻይና፤ ኢራን የሀውቲዎችን ጥቃት እንድታስቆም ጫና እያሳደረችባት ነው ተባለ
ሀውቲዎች የሚፈጽሟቸው ጥቃቶች በብዛት በቻይና ጥቅም ላይ የሚውለውን በእስያና አውሮፖ መካከል ያለውን ዋና መተላለፊ በማስተጓጎል የጉዞ ወጭ እንዲጨምር አድርጓል
የቻይና ባለስልጣናት ኢራን የሀውቲዎችን ጥቃት ካላስቆመች ከቤጂንግ ጋር ያላት የንግድ ግንኙነት አደጋ ውስጥ እንደሚገባ ገልጻለች ተብሏል
ቻይና፤ ኢራን የሀውቲዎችን ጥቃት እንድታስቆም ጫና እያሳደረችባት ነው ተባለ።
የቻይና ባለስልጣናት በኢራን የሚደገፉት የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት እንዲስቆሙላቸው የኢራን አቻቸውን መጠየቃቸውን ለጉዳዮ ቅርቡ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
የቻይና ባለስልጣናት ኢራን የሀውቲዎችን ጥቃት ካላስቆመች ከቤጂንግ ጋር ያላት የንግድ ግንኙነት አደጋ ውስጥ እንደሚገባ ገልጻለች ተብሏል።
ሀውቲዎች በሚሰነዝሩት ጥቃት እና በንግድ ጉዳይ በቴህራን እና በቤጂንግ በቅርብ በተካሄዱ በርካታ ስብሰባዎች መነሳታቸውን የኢራን ምንጮች መግለጻቸውን ዘገባው ጠቅሷል።
"በመሰረቱ ቻይና እንዳለችው 'የኛ ፍላጎት በየትኛዉም መንገድ የሚጎዳ ከሆነ፣ ከቴህራን ጋር ባለን ንግድ ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል። ስለዚህ ሀውቲዎች ጥቃት ከማድረስ እንዲታቀቡ ንገሯቸው" ሲል አንድ ሰሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ እና በውይይቱ ላይ የተሳተፈ የኢራን ባለስልጣን ለሮይተርስ ተናግሯል።
ሀውቲዎች ለፍልስጤማውያን አጋርነት ለማሳየት ነው በማለት የሚፈጽሟቸው ጥቃቶች በብዛት በቻይና ጥቅም ላይ የሚውለውን በእስያና አውሮፖ መካከል ያለውን ዋና መተላለፊ በማስተጓጎል የጉዞ ወጭ እንዲጨምር አድርጓል።
ነገርግን ቻይና በዚህ ጉዳይ በይፋ አስተያየት አለሰጠችም።
ባለፈው አስር አመት ቻይና የኢራን ዋና የንግድ አጋር ብትሆንም አሁን ላይ እየተቀዛቀዘ መጥቷል።
በአሜሪካ ማዕቀብ ምክንያት በርካታ የነዳጅ ደንበኞች የራቋት ኢራን፣ ባለፈው አመት 90 በመቶ የሚሆነውን ድፍድፍ ነዳጇን የገዟት የቻይና ነዳጅ አጣሪ ኩባንያዎች መሆናቸውን የታንከር ትራኪንግ መረጃ ያመለክታል።
የኢራኑ ባለስልጣን እንደተናገሩት የቻይና የሆነ መርከብ የሚጎዳ ከሆነ ልትከፋ እንደምትችል ገልጽ አድርጋለች።