ከአስከሬን ሳጥን አንኳኩተው የወጡት አዛውንት ከሳምንት በኋላ ህይወታቸው አለፈ
በኢኳዶር “ሞተዋል” ተብለው ሊቀበሩ የነበሩት የ76 አመት አዛውንት በአስከሬን ሳጥን ውስጥ በህይወት መገኘታቸው ይታወሳል
አዛውንቷ ከሳምንት በኋላ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ መሞታው በሐኪም ከተረጋገጠ በኋላ አስከሬናቸው ሳጥን ውስጥ ተከቷል
በሳለፍነው ሳምንት በኢኳዶር “ሞተዋል” ተብለው ሊቀበሩ የነበሩት የ76 አመት አዛውንት በአስከሬን ሳጥን ውስጥ በህይወት መገኘታቸው አነጋጋሪ ክስተት ነበር።
የ76 አመቷ ቤሊያ ሞንቶያ “ህልፈታቸው” በሀኪሞች ተረጋግጦ ነበር አስከሬናቸው የሬሳ ሳጥን ውስጥ ገብቶ የነበረው።
ለ”ሟቿ” ልብስ ለመቀየር ወደ ሳጥኑ የተጠጉ ቤተሰቦችም ድምጹን ብቻ ሳይሆን አዛውንቷ ትንፋሿ እንዳልተቋረጠ አረጋገጡ።
እናም በፍጥነት ወደህክምና ተቋም ተወስደው ለቀብር የተሰባሰበው ቤተሰብም ወደየመጣበት ተመልሷል።
“ህልፈታቸው” በሀኪሞች ተረጋግጦ ቤተሰቡ ከተረዳ ከአምስት ስአት በኋላ ሳጥን ውስጥ በህይተ የተገኙት አዛውንቷ ለአንድ ከሳጥን ከወጡ በኋላ ለአንድ ሳምንት በህይወት መቆየት ችለዋል።
አዛውንቷ ከሬሳ ሳጥን ውስጥ ከወጡ በኋላ በሆስፒታል ለሳምንት ያክል መቆየት ችለው የነበረ ሲሆን፤ ከሰባት ቀናት በኋላ ጋድመ ወዳመለጡት ሞት ተመልሰው መሄዳቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።
በዚህኛው ዘዙር አዘውንቷ መሞታቸው ከጤና ባለሙያዎች በተጨማሪ በሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ከተረጋገጠ በኋላ አስክሬናቸው ሳጥን ውስጥ እንገባ መደረጉም ነው የተነገረው።
እናቱ በህይወት መገኘታቸውን ተከትሎ፤ እናቱ ጤናቸው እንዲመለስ በመጸለይ ላይ የነበረው ልጃቸውጊልበር ሩዶልፎ፥ “አሁን እናቴ መሞቷ እርግጥ ነው” ሲል አረጋግጧል።
ቢኳዶር የተፈጠረው ክስተት ህይወታቸው ማለፉ ተነግሮ በፍጥነት ወደ አስከሬን ሳጥን የተወረወሩና የሚያደምጣቸው አጥተው ነፍሳቸው ሳይወጣ የተቀበሩ ሰዎች ቁጥር ቀላል እንደማይሆን ያሳያል ተብሏል።