ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ማህበረሰባቸውን ከከባድ ወንጀለኞች ለመጠበቅ በሚል የሞት ቅጣትን ያሳልፋሉ
የሞት ቅጣት በባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ (የሃሙራቢ ህግ) ከተካተተበት ጊዜ ጀምሮ በህግ እውቅና ተሰጥቶት ተፈጻሚ መሆን መጀመሩ ይነገራል።
የሞት ፍርድን ተፈጻሚ በማድረግም ጥንታዊቷ ግብጽ (ከክርስቶስ ልደት በፊት በ2627 ዓመተ አለም) ቀዳሚዋ መሆኗን የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ።
የሀገር ክህደት፣ ስለላ፣ አሰቃቂ ግድያ፣ ሽብርተኝነት፣ አስገድዶ መድፈር፣ አፈና፣ ሕገወጥ የሰዎችና እጽ ዝውውር እንዲሁም ከባድ የሙስና ወንጀልም የሞት ፍርድን ከሚያስከትሉት መካከል ይጠቀሳሉ።
የሞት ቅጣት የሰውን ልጅ ክቡር ህይወት የሚያሳጣ መሆኑን የሚጠቅሱ የመብት ተከራካሪዎች የሞት ፍርድን ይቃወማሉ።
የሚፈጸሙት ወንጀሎች አሰቃቂነትን እና የሀገርና ዜጋውን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ መሆናቸውንና አስተማሪ እርምጃ ካልተወሰደ ስርአት አልበኝነት ይነግሳል የሚሉት ደግሞ ቅጣቱ ተፈጻሚ እንዲሆን ይደግፋሉ።
ከ18ኛው ክፍለዘመን ወዲህ በርካታ የዓለም ሀገራት አወዛጋቢውን የሞት ፍርድ መሰረዛቸውን የወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው መረጃ ያሳያል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ የሚከተሉት የአፍሪካ ሀገራት ግን ማህበረሰባቸውን ከከባድ ወንጀለኞች ለመጠበቅ በሚል የሞት ቅጣትን ያሳልፋሉ።