በማድግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚውል 'የአየር ንብረት ፈንድ' እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ ተደረሰ
አረብ ኢምሬትስ ለፈንዱ 100 ሚሊዮን ዶላር ለማዋጣት ቃል ገብታለች
በዱባዩ የኮፕ28 ስብሰባ ፈንዱ ወደ ስራ እንዲገባ ስምነት ላይ የተደረሰው በግብጿ ሻርም አል ሼህ ከተማ በተካሄደው የኮፕ27 ስብሰባ እንዲቋቋም ከተወሰነ ከአንድ አመት በኋላ ነው
በማድግ ላይ ላሉ ሀገራት የሚውል 'የአየር ንብረት ፈንድ' እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ ተደረሰ።
የኮፕ28 ስብሰባ ፕሬዝደንት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የበለጠ ተጎጂ ለሆኑ ሀገራት የሚውል 'የአየር ንብረት ፈንድ' እንዲንቀሳቀስ ሀገራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታውቀዋል።
የአረብ ኢምሬትስ አመራር ተጋላጭ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ሀገራት እንዲረዱ በማድረግ አለምአቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ጥረቶች እንዲጠናከሩ እየሰራ መሆኑን ፕሬዝደንቱ ገልጸዋል።
የአረብ ኢምሬትስ የኢንዱስትሪ እና አድቫንስድ ቴክኖሎጂ ሚኒስትር እና የክፕ28 ስብሰባ ፕሬዝደንት ዶክተር ሱልጣን ቢን አህመድ አልጃብር ዘላቂ የኢኮኖሚ ልማትን ለማሳካት ተጋላጭ የሆኑ ሀገራት እና ማህበረሰቦች እንዲረዱ በተነሳሽነት ብዙ እርምጃዎችን መወሰዳቸውን ተናግረዋል።
የኢምሬትስ ዜና አገልግሎት(ዋም) እንደዘገበው ዶክተር አልጃብር ይህን ያሉት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ በማደግ ላይ ላሉ ሀገራት ከአየር ንብረት ፈንዱ እንዲረዱ ወሳኝ የተባለ ስምምነት በተደረሰበት እና ፈንዱን በተመለከት እዚህ ደረጃ እንዲደረስ ያደረጉ ግለሰቦችን ባመሰገኑበት ወቅት ነው።
ፈንዱ ወደ ስራ እንዲገባ ስምነት ላይ የተደረሰው በግብጿ ሻርም አል ሼህ ከተማ በተካሄደው የኮፕ27 ስብሰባ እንዲቋቋም ከተወሰነ ከአንድ አመት በኋላ ነው።
አረብ ኢምሬትስ ለፈንዱ 100 ሚሊዮን ዶላር ለማዋጣት ቃል ገብታለች።
የኮፕ28 ፕሬዝደንት ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ባደረጉት ጥሪ ጀርመን 100 ሚሊዮን ዶላር፣ እንግሊዝ 50 ሚሊዮን ዶላር፣ ጃፖን 10 ሚሊዮን ዶላር እና አሜራካ 17.5 ሚሊዮን ዶላር ለፈንድ ለማዋጣት ቃል ገብተዋል።
በኮንፈረንሱ የመጀመሪያ ቀን በኮፕ28 ፕሬዝዳንት አማካኝነት 726 ሚሊየን ዶላር ለመለገስ ቃል የተገባ የገንዘብ መጠን ሲሆን፤ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ልዩ የሆነ ዓለም አቀፍ ፈንድ ለማንቀሳቀስ በተደረገው ታሪካዊ ስምምነት ነው።
ፈንዱን ለማቋቋም ስምምነት ላይ የተደረሰው በግብጽ ሻርም አልሸህ በተካሄደው የኮፕ27 ሰብሰባ ሲሆን በዱባዩ ስብሰባ ፈንዱ እንዲንቀሳቀስ ስምምነት ላይ ደተደረሰ።