ሴቶች በአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ ተጎጂ ናቸው ተባለ
በማራካሽ ሞሮኮ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ ተካዷል
በዓመታዊ ስብሰባው የሴቶችና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ትኩረት አግኝቷል
በማራካሽ ሞሮኮ በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት እና ዓለም ባንክ ዓመታዊ ስብሰባ የሴቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት አግኝቷል።
ጉዳዩ የተነሳው ከዓለም ባንክ ተወካዮች፣ ከነጋዴዎች፣ ከአየር ንብረት መሪዎች፣ ከስርዓተ-ጾታ እኩልነት እና የአየር ንብረት ፍትህ ተሟጋቾች ነው።
ከጉባኤው ጎን ለጎን "የአፍሪካ ሴቶች እምቅ አቅም እና ለልማት ያላቸው ትልቅ አስተዋጽዖ” በሚል ርዕስ አህጉሪቱ ላይ ያተኮረ ስብሰባ ተካሂዷል።
በስብሰባው ላይም ሴቶች በአየር ንብረት ለውጥ የበለጠ ተጎጂ መሆናቸው ተመላክቷል
አፍሪካ በወጣቶች፣ በተፈጥሮና ማዕድን ሀብት፣ በኢንዱስትሪ፣ በግብርና እና በሌሎችም ዘርፎች ያላትን ግዙፍ አቅም በስብሰባው ጎልቶ ታይቷል።
እንደ ሞሮኮ ያሉ ሀገራትም ትልቅ የዓለም ገበያ እንደሚሆኑ የተጠቆመ ሲሆን፤ በተለይም በኢንዱስትሪና በዲጂታል ዘርፍ ተስፋ ሰንቃለች።
በሞሮኮ ማራካሽ ከተማ ለአንድ ሳምንት ያህል ከተካሄደው የድርጅቶቹ ዓመታዊ ስብሰባ ጎን ለጎን የአፍሪካ ሴቶች ስራ ፈጣሪዎች የግል ዘርፍ ጥምረት በአፍሪካ ሴቶች ስራ ፈጣሪዎች ኔትወርክ እና በተመድ ሴቶች ጋር ትብብር ተመስርቷል።